News

 • የአዳማ ነጋዴዎች በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተቃወሙ

   

   

  ማስታወቂያዎቹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ካልተስተካከሉ ሰሌዳ መንቀል ይጀመራል

  “አማርኛን ከክልሉና ከከተማው ለማጥፋት የሚደረግ ጥረት ነው” ነጋዴዎች

  “ብሔሮችን እርስ በርስ ለማጋጨት ሆን ተብሎ የሚነዛ አሉባልታ ነው” የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

                   ለንግድ ድርጅቶቻቸው በሰቀሏቸው ማስታወቂያዎች ላይ የተወሰደው በቀይ ቀለም የማበላሸት እርምጃ ህገወጥ ነው ያሉት የአዳማ ከተማ ነጋዴዎች፤ በማስታወቂያዎቹ ላይ “ኦሮምኛ ፊደላት አነሱ” በሚል ሰበብ አማርኛን ከክልሉና ከከተማው ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ እርምጃውን ተቃወሙ፡፡ የአዳማ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ፤ አብዛኛዎቹ ማስታወቂያዎች ያለባቸው እግር እንዲስተካከል በተለያየ መንገድ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁሞ፣ ነጋዴዎቹ እርማት ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በ900 ማስታወቂያዎች ላይ በቀይ ቀለም የ“X” ምልክት ማድረጉን ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ማስታወቂያዎቹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ካልተስተካከሉ ሰሌዳዎችን የመንቀል እርምጃ ይወስዳል ብሏል ቢሮው፡፡ “ለረጅም አመት የተጠቀምንበትን ማስታወቂያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ብልሽትሽቱን የሚያወጡት” ያለው አንድ ወጣት ነጋዴ፤ እርምጃው አማርኛን ከክልሉና ከከተማው ለማጥፋት የሚደረግ ጥረት ነው ሲል ነቅፏል፡፡

  ከዚህ ቀደምም ቢሮው ከዘጠኝ ሺህ በላይ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን ከየንግድ ቤቱ ነቅሎ ወስዶ የት እንዳደረሰው አይታወቅም ብለዋል ሌላው የአዳማ ነጋዴ፡፡ “ነጋዴው ህግና ስርዓትን ተከትሎ እየሰራ ለመንግስት ተገቢውን ግብር እየከፈለ ነው” ያሉት አንድ አስመጪና ላኪ በበኩላቸው፤ “የአማርኛ ፊደል በዛ፣ የኦሮምኛው ደቀቀ እያሉ መጥፎ መንፈስ የሚዘራ ስራ ከመስራት ህገ ወጥ ንግድንና ነጋዴን ስርዓት በማስያዝ፣ ለምን ጤናማ የንግድ ውድድር እንዲፈጠር አያደርጉም?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ “ነጋዴው የማስታወቂያ ሰሌዳውን በውድ ዋጋ አሰርቶ እንደሚያቆመው እየታወቀ ያለማስጠንቀቂያ በቀይ ቀለም ማበላሸት ነጋዴውን ለመጉዳትና ሞራሉን ለመንካት ሆን ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነው” ያሉት ሌላ ነጋዴ፤ ማስታወቂያውን ለማበላሸት የወጣው ቀይ ቀለም ለመንግስትም ቢሆን ኪሳራ ነው ብለዋል፡፡

  ላለፉት 28 ዓመታት በንግድ ስራ ላይ እንደቆዩ የጠቆሙ አንድ ነጋዴ እስከዛሬ፣ ከማስታወቂያ ጋር በተያያዘ ያየሁት አንድም ችግር የለም በማለት የአሁኑ ፖለቲካዊ ዓላማ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ግንታቸውብ ሰንዝረዋል፡፡ “ጉዳዩ በቅርቡ ከተነሳው የተማሪዎች አመፅ ጋር የተያያዘና አንዳንድ ወገኖች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ጥላቻ ለማሳየት የተጠቀሙበት አጋጣሚ ሳይሆን አይቀርም” ብለዋል - ነጋዴው፡፡ የአዳማ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘውዴ የሺጥላ በበኩላቸው፤ በየንግድ ቤቱ በር ላይ የተሰቀሉት ማስታወቂያዎች መሰረታዊ ችግር እንዳለባቸው ጠቅሰው ከእነዚህም ውስጥ የመጀመሪያው በኦሮምኛ ቋንቋ የተፃፉት ሁሉም ማስታወቂያዎች በጣም ደቃቃና ለማንበብ አስቸጋሪ መሆናቸው ነው ብለዋል፡፡ ሁለተኛው ችግር የአማርኛውን ቃል ወደ ኦሮምኛ አስተርጉመው ሲፅፉ የትርጉም መፋለስ ማስከተሉ የክልሉ የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ በመሆኑ የተፋለሰውን እንዲያስተካክሉ እርምጃው መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

  ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ባህልና ቱሪዝም ቢሮው የማስታወቂያ ፅሁፋቸውን እንዲያስተካክሉ በኦሮሚያ ቴሌቪዥንና በተለያዩ መንገዶች ጥሪ ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆሙት አቶ ዘውዴ፤ ነጋዴዎች ይህን የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከዘጠኝ መቶ በላይ በሆኑ ማስታወቂያዎች ላይ በቀይ ቀለም የ “X” ምልክት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ “ነጋዴዎቹ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተጠቀሱትን ችግሮች ለማስተካከል ካልቻሉ ቀጣዩ እርምጃ ማስታወቂያዎቹን መንቀል ይሆናል” ያሉት የቢሮው ሃላፊ፤ ባለፈው ዓመትም ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ አስተካክሉ ብለን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ቢሮው ከ10 ሺህ በላይ ማስታወቂያዎችን ነቅሎ ከወሰደ በኋላ፣ አስተካክለው እንዲወስዱ ጥሪ ቢያደርግም የመጣ ባለመኖሩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎቹ ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል ብለዋል፡፡ አማርኛን ከክልሉ ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ ነው የሚለውን የነጋዴዎች ቅሬታ በተመለከተም፤ “የክልሉ የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ በመሆኑ በአግባቡ ተጠቀሙ አልን እንጂ አማርኛን አትጠቀሙ አላልንም” ያሉት አቶ ዘውዱ፤ ይሄ ሆነ ተብሎ ብሄሮችን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚነዛ አሉባልታ ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

  “ ጉዳዩን ከሰሞኑ የተማሪዎች ብጥብጥ ጋር ለማገናኘት መሞከሩም ብዙ ርቀት የማያስኬድ የፅንፈኞች አሉባልታ ነው” ብለዋል - ሃላፊው፡፡ የአዳማ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን አንዱ የክልሉን ባህል፣ ቋንቋና ትውፊት ሳይበረዝና ሳይበላሽ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዘውዱ፤ አሁን እየተደረገ ያለው ግን ቋንቋና ባህልን ማበላሸት ነው ብለዋል፡፡ ‹ሚኒ ማርኬት› የሚለውን ማስታወቂያ በኦሮምኛ የላቲን ቁቤ ‘ሚኒ ማርኬት’ ብለው ሲያስቀምጡት ‘ሚኒ’ የሚለው ቃል በኦሮምኛ አስነዋሪ ቃል ስለሆነ፣ ‹ይህን አስተካክሉ› ብሎ መንገር ወደ ሌላ ነገር መተርጎም የለበትም ያሉት ሃላፊው፤ እስካሁን ምልክት ከተደረገባቸው ከዘጠኝ መቶ ማስታወቂያዎች ውስጥ 300 ያህሉ ማስተካከያውን እንዳደረጉ ጠቁመው፤ ሌሎቹም እንዲያስተካክሉ እየተጠበቁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከአንድ ሳምንት በኋላ ሰሌዳ የመንቀል እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቀቀዋል - የቢሮው ሃላፊ፡፡

   

  Read more
 • ቴዲ አፍሮና ውዝግብ ያልተለየው ዝና

   

  በአዲስ አበባ ታትሞ ከተሰራጨው ቁምነገር መጽሔት የተወሰደ

  ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ወደ ሙዚቃው ዓለም ተቀላቅሎ ወደ ዝና ማማ መውጣት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ መነጋገሪያ ከመሆን ያመለጠ አርቲስት አይደለም፡፡ በ1993 ዓ.ም ማብቂያ ላይ ባወጣው የመጀመሪያ ‹አቦጊዳ› አልበሙ የሙዚቃ አድማጩን ጆሮ ለመቆጣጠር የቻለው ቴዲ አፍሮ በወቅቱ በአለቤ ሾው ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ቀርቦ ‹25 ዓመቴ ቢሆንም ፍቅረኛ ገና አልያዝኩም › ባለ ማግስት የከተማው ወጣት ሴቶች አይን ማረፊያ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚሁ ይፋ ካልወጣ የሴቶች አደን ጋር ተያይዞ የመጀመሪያውን ውዝግብ አስተናገደ፡፡ ‹በሴት ልጅ ጡት ላይ ፊርማ ፈርሟል› በሚል ተሰራጨው ወሬ ከከተማ ወሬነት አልፎ የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ገበያ መጥሪያና ማሻሻጪያ ሆኖ ነበር፡፡‹የተባለውን ነገር አላደረኩም፤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ኩሩዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር እንዳደርግ አይጠይቁኝም ፤ እኔም አላደረኩትም› ብሎ በወቅቱ ለታተመችው ቅፅ 1 ቁጥር 1 ቁም ነገር መፅሔት ላይ ቢናገርም አድናቂዎቹን ከማሳመን በቀር የወሬ ማጣፈጫነቱን አላስቀረውም ነበር፡፡

  ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ውዝግቡን በዚሁ መልኩ ለመቋመጨት ጥረት ቢያደርግም ከዚሁ አልበሙ በፊት በሰራው የመጀመሪያ ካሴቱ ሳቢያ ለሌላ ውዝግብ የተዳረገው ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱን ሳያወጣ ለዓመታት አስቀምጦት የነበረው ቮይስ ሙዚቃ ቤት የአቦጊዳ አልበሙ የአድማጭን ጆሮ መቆጣጠር ተመልክቶ አዲሱን አልበም ለገበያ ያቀረበው ወዲያውኑ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ‹የአቦጊዳን አልበም ሽያጭ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለበሁበት ደረጃ ፈፅሞ የማይመጥን› ያለውን ከዓመታት በፊት የተሰራውን ካሴት ‹ሳያስፈቅደኝ መልቀቅ የለበትም› በሚል ሌላ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ ተፈጠረው ውዝግብ መሀል ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ገብቶ በሽምግልና ጉዳዩን እንዲፈታ እስኪያደርግ ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ነበር፡፡

  ቴዲ በሙዚቃ ስራው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ህይወቱና በሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶቹ ዝናውን ከፍ እያለ ቢመጣም ምርጫ 97 ተከትሎ ገበያ ላይ በዋለሁ ሶስተኛ ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ ሳቢያ ውዝግቡ ከግለሰብ ወደ መንግስት ዞሮ ነበር፡፡ ይፋዊ በሆነ መንገድ መንግስት ተቃውሞውን ባይገልፅም ዘፈኑ በማንኛውም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዳይተላለፍ ከመከልከል ጀምሮ ለጉዳዩ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ በመስጠት የውዝግቡን ጡዘት እንዳከረረው እናስታውሳለን፡፡ ከምርጫው ጋር የተያያዘው ውጥረት ቀስ እያለ ቢረግብም ከመንግስት ጋር ያለው ውዝግበ ከአንድ ዘፈን ወደ ሶስት አድጎ ከ‹ካብ ዳህላክና› እና ‹ሼ መንደፈርን› ጨምሮ ታይቷል፡፡ መንግስት በወቅቱ ከነበረው ፖለቲካዊ ራስ ምታት ተረጋግቶ ሚሊኒየሙን ለመቀበል ሽር ጉድ በሚልበት ወቅት ቴዲ አሁንም የህዝቡን የልብ ትርታ ያዳመጠ ‹አበባ አየሽ ሆይ› የተሰኘውን ተወዳጅ ባህላዊ ዜማ ለእርቅ አውሎት ብቅ አለ፡፡ ከፓለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር ተያይዞ የእርቅ መንፈሱ በሁሉም ሙዚቃ አድማጭ ጆሮ ማንቃጨል ቢጀምርም መንግስት ግን ዘፈኑን ዘወትር በየሚዲያው ላይ ሲለቀቅ ሁኔታውን በዝምታ ከመመልከት ውጪ ‹ሆ በል ከበሮ ሆ በል አንተ ማሲንቆ ስታይ ሰው ታርቆ› በሚለው ስንኝ ከህዝቡ ጋር እስክስታ ለመውረድ ሳይችል ቀርቷል፡፡የቴዲ አፍሮ የእርቅ መንፈስ ሚሊኒየሙን ብቻ ሳይሆን ባህር ማዶ ተሻግሮ ለመዝፈንና ለማስጨፈር ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ከሚሊኒየሙ ጋር ታኮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቢዮንሴ ኖውልስ በቴዲ አፍሮ ‹አበባ አየሽ ሆይ› ዜማ ወገቧን ይዛ ስትጨርፍር ታይታለች፡፡

  ቴዲ በዘፈኑ የሀገሩን ልጆች አልፎ የውጪ ሰዎችን ማማለል ቢችልም ከመንግስት ጋር የገባው ውዝግብ ከዚህ ቀደም ከግለሰቦች ጋር እንዳለው አይነት ተራ የሚባል አልነበረምና ወደ እስር ቤት የሚገባበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በብዙዎቹ አድናቂዎቹ ዘንድ አሁንም ድረስ እንደሚታመነው ‹ቴዲ አፍሮ በመኪና ሰው ገጭቶ አምልጧ› የሚለውን የአቃቤ ህግ ክስ ለመቀበል ዳግም መወለድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላል፡፡ ‹ደጉ ይበልጣል› የተባለውን የ18 ዓመት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ስለመግደሉና ስለማምለጡ በወቅቱ መነጋገሪያ የነበረው ክስ ከብዙ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ምልልስ በኋለ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ሲቋጭ ‹ቴዲ እንደ በፊቱ ተወዳጅ ሥራዎቹን ይሰጠን ይሆን ›የሚል ጥርጣሬ መኖሩ አልቀረም፡፡ የፈጠራ ስራ ችግር የሌለበት ቴዲ ከእስር ቤት በወጣ በሶስተኛው ወር ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን በልመና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች ማቋቋሚያ አደረገ፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይም ያገኘውን ከአንድ ሚሊየንም ብር በላይ ገንዘብም ለኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር አስረከበ፡፡

  ከሚያወጣቸው አልበሞች ጋር ተያይዞ ውዝግብ የማያጣው ቴዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋርም ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዘፈኖች መመሳሰል ጋር በተያያዘ በሰይፉ ፕሮግራም ላይ በቀረበ ዘገባ ሳቢያ ጉዳዩ በስምምነት እስኪፈታ ድረስ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ቴዲ የሌሎቹን ያህል አይሁን እንጂ ከረዥም ጊዜ ማናጀሩ አዲስ ገሠሠ ጋርም ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የተለያዩ ሲሆን በተደጋጋሚ ተሰርቀው በወጡ ነጠላ ዜማዎቹ ሳቢያም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የቴዲ አራተኛ ካሴትም ውዝግብ መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ‹ጥቁር ሰው› በሚል ርዕስ ያወጣው አልበም ከፍተኛ የሙዚቃ ችሎታውን ያሳየበትና አዳዲስ የአዘፋፈን ስልቶችን ያካተተበት ሥራው ቢሆንም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፓለቲካዎ አቋም ጋር ተያይዞ ተቃውሞ የገጠመው ወዲያውኑ ነበር፡፡ ጉዳዩ ከታሪክ አንፃር መታየት ያለበትና የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር በሚል የተሰራ ሙዚቃ እንደሆነ የተለያዩ ሰዎች የየራሳቸውን አስተያየት በማከል በየመገናኛ ብዙሃኑ ላይ ለመከራከር መሞክሩም ፓለቲካዊ መልክ የተሰጠውን ውዝግብ ለማብረድ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ከዚህ ውዝግብ ቀጣይ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ‹ወደ ፍቅር ጉዞ› የሚል ስያሜ የተሰጠው የሙዚቃ ኮንሰርትም በበደሌ ቢራ ስፖንሰር አድራጊነት ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ክልሎች በመጓዝ ለማሳየት ፕሮግራም ቢዘረጋም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ተያይዞ ‹ሰጠ› በተባለ ቃለ ምልልስ ሳቢያ በደሌ ቢራ ኮንሰርቱን ሰርዞታል፡፡ በደሌ ኮንሰርቱን ለመሰረዝ ምክንያት የሆነው ቴዲ ሰጠ በተባለው ቃለ ምልልስ ሳቢያ የተቆጡ ወገኖች ‹በደሌ ቢራን እንዳይጠጡ!› የሚል የቅስቀሳ ዘመቻ በመጀመራቸው እንደሆነና ከንግድ ስራ አንፃር ኮንሰርቱን መሰረዝ አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ቴዲ የተባለውን ቃለ ምልልስ እንዳልሰጠ፤ ይልቁንም በመፅሔቱ የተፈጠረ ተራ ስህተት እንደሆነ ገልጾ ለመከራከር ቢሞክርም ሰሚ
  ያገኘ አይመስልም፡፡ ጉዳዩ ስር እየሰደደ የመምጣቱ አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወደሰደውም የዘመቻው ቀስቃሾች የቴዲን ኮንሰርት በማሰረዝ ብቻ ሳይገቱ ሌላም የመልስ ምት መሰጠት እንዳለበት የሚያሳስቡ ቅስቀሳዎች ተጠናክረው በመሰጠታቸው የጥቁር ሰው ተነፃፃሪ ተቃራኒ ነጠላ ዘፈን በአንድ አርቲስት
  ተሰርቶ ተለቋል፡፡

  ይህ የውዝግብ አዙሪት ባልተቋጨበት ሁኔታ ኮካ ኮላ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ በየሀገሩ ከሚያሰራቸው አርቲስቶች መሀከል አንዱ አድርጎ ቴዲን እንደመረጠው ተሰማ፡፡ቴዲም ከሶስት ወራት በላይ በአዲስ አበባና በኬኒያ እየተመላለሰ የሙዚቃ ስራውን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ ተነግሯል፡፡ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በማድረግ እንደተለመደው ግዙፍ የቢዝነስ ተቋም የሆነው ኮካ ኮላ በተለያዩ ድምጻውያን ሙዚቃዎችን አዘጋጅቶ ራሱን እያስተዋወቀ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ የተሰሩት በብዙ ዓይነት ቋንቋዎችና ከተለያዩ ሀገራት በተውጣጡ ድምጻውያን ሲሆን የተቀረጹት በኮካኮላ ስቱዲዮ /Coke Studio/ ነው፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የተመረጡ ድምጻዊያን የሠሩት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አፊሲያላዊ የኮካ ኮላ ሙዚቃ ‹‹The world Is our›› /አለም የኛ ናት/ የሚል ርዕስ አለው፡፡ ይሄንን ሙዚቃ በድምፅ ለመስራት ከተመረጡት በርካታ ዘፋኞች መካከል ኢትዮጵያዊው ቴዲ አፍሮ ይገኝበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ አካባቢ ቴዲ ለሙዚቃ ኮንሠርት ወደ ኳታር ባቀናበት ወቅት ከኮካ ኮላ ካምፓኒ ስልክ ተደውሎ በዓለም ዋንጫው ሙዚቃ ላይ እንዲሳተፍ ተጠየቀ፡፡ በዚህ መሠረት ከሌሎች አፍሪካውያን ድምጻውያን ጋር በጋራ ካቀነቀነው ዘፈን በተጨማሪ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራና በግሉ የተሳተፈበት ሙዚቃ በኮካ ኮላ ስቱዲዮ መቀረጹ ተነገረ፡፡ ሙዚቃውም በ2014 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለህዝብ እንደሚቀርብ ተገልጾ ነበር፡፡ ይሁንና በተባለበት ጊዜ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አልተለቀቀም፡፡

  በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን የተሰሩ ዘፈኖች ግን በይፋ ተለቀው እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራው የቴዲ ዘፈን ግን መዘግየቱ ሳያንስ በቅርቡ ደግሞ ሙዚቃው ከነአካቴው ከስቱዲዮ እንደማይወጣ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ቴዲ አፍሮ በድረገጹ ላይ ወጣ በተባለ ጽሁፍ ድርጊቱን ኮነነ፡፡ የኮካ ኮላ ካምፓኒ ድርጊት ‹‹ሀገራችን ያዋረደ›› ጭምር መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚከታተለው ገለጸ፡፡ የኮካ ኮላ ዘመቻ በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚታወቀው ኮካ ኮላ በዓለም ላይ 200 ከሚበልጡ ሀገሮች ውስጥ ፋብሪካውን ተክሎ በቀን ከ1.7 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ጠርሙስ ኮካ ይሸጣል፡፡ መመረት የተጀመረበትን 128 ኛ ዓመት በማክበር ላይ ያለው ኮካ ኮላ ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት ባለው ሶስት ወራት ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል፡፡ ኮካ ኮላ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ተቃውሞዎች ገጥመውት የሚያውቁ ሲሆን ሁሉንም በማይበገረው የገንዘብ ሀይሉ አሸናፊነቱን አረጋግጦ ነው የተወጣው፡፡ ከአረብ እስራኤሎች ጦርነት በኋላ በአረቡ ዓለም በታየው የፀረ እስራኤል ዘመቻ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአብዛኛዎቹ አረብ ሀገራት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ለፍልስጤሞች ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ጥረዋል፡፡ አረቦቹ ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ብቻ ሳይወሰኑ ፊታቸውን ወደ ፔፕሲ አዙረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ዘመቻ የኮካ ኮላን ገበያ የሚፈታተንና ከገበያ የሚያስወጣ ስላልነበረ በማስታወቂያው ላይ ባፈሰሰው ከፍተኛ በጀት የዓለማችን ቀዳሚ ለስላሳ መጠጥነቱን አስከብሮ ለመቆየት ችሏል፡፡ እ.እ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይም የህንድ ገበሬዎች ኮካ ኮላ ለማሳችን የሚያስፈልገንን ውሃ ተሸማብን በማለት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ተቃውሟቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በዓመት 11 ቢሊዮን ዶላር ለማስታወቂያ ብቻ የሚያወጣው ኮካ ኮላ ንፁህ የመጠጥ ውሃን በማውጣትና ዙሪያ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚመድበውን ማህበራዊ በጀት ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር በማሳደግ ራሱን ከህንድ አርሶ አደሮች ዘመቻ ተከላክሏል፡፡

  የኮካ ኮላ የአቀማመም ምስጢር ድብቅነቱን ተከትሎ ሱስ አስያዥ ቅመም እንዳለውና ለጤናም አደገኛ ስለመሆኑ የተወራበት ጊዜ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶም ሰዎችን ሱስ የሚያሲይዝ የኮኬይን ቅመም እንዳለው ሲነገር ኮካ ኮላ ግን ይህ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡ያም ሆኖ ኮካ ኮላ አሁንም
  ድረስ በብዙ ሀገሮች ውስጥ ተወዳጅ መጠጥ ቢሆንም እንደ ሰሜን ኮሪያ በርማና ኩባ አይነት ሀገሮች ኮካ ኮላ ፋብሪካ በሀገሮቻቸው እንዲቋቋም ያልፈቀዱ ሀገራት ናቸው፡፡እ.ኤ.አ በግንቦት 8 ቀን 1886 በአትላንታ ጆርጂያ ለራስ ምታት መድሃኒት ይሆናል ብሎ መድሃኒት ቀማሚው ጆን ኤስ ቴምበር ከካካዋ ፍሬ በሶዳ ውሃ በጥብጦ ያዘጋጀው ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ ይኸው ዛሬ በመላው ዓለም ይጠጣል፡፡ በወቅቱ ድካምንና ራስ ምታትን እንዲሁም ድብርትንና የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ያነሳሳል በሚል የተቀመመው ኮካ ኮላ በአዲስ መልኩ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምስጢራዊነቱን ጠብቆ መመረት ከጀመረ እነሆ ዘንድሮ 120 ዓመታት ሆኖታል፡፡
  ዘመቻ ‹‹ኮካ አትጠጡ››የድምጻዊው አድናቂዎችና በሁኔታው ስሜታችን ተነክቷል ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ድረገፆች አማካኝነት በኮካ ኮላ ካምፓኒ ላይ መቀየማቸውን የሚያሳዩ ምስሎችንና ጽሁፎችን ለጠፉ፡፡ የካምፓኒውን ምርቶች ባለመጠጣት ተቃውሞአቸውን ለማሰማት ዛቱ፡፡ በተግባር ጉዳዩ ለመፈጸሙ
  ማረጋገጫ ባናገኝም በቴዲና በኮካ ኮላ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አበሳጭቷቸው ከኮካ ምርቶች የታቀቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ግን አያዳግትም፡፡ በተለይ በማህበራዊ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ሲጻፍ የነበረውን ‹‹ፀረ-ኮካ›› ዘመቻ የቅስቀሳ መልዕክቶች ስንመለት የተባለው ድርጊት መጨረሻው የት ነው እንድንል ይገፋናል፡፡ የሙዚቃው አለመለቀቅ ‹‹ሀገራችን ከመናቅ›› የመጣ ነው ከሚል ሀሳብ ጋር አያይዞ ድምፃዊው ቅሬታውን መግለጹ ተቃውሞውን እንዲደምቅ አድርጎታል፡፡ በቴዲ አፍሮ የግል ድረገጽ ላይ ወጣ የተባለው መግለጫ እንዲህ ይላል፡፡‹‹ስለ ዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ
  የተሰጠ መግለጫ ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ›› ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ ሚርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ሲደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ ግንኙነቱን ሚጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባ እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀወው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው የቴዲ ከኮካ ጋር ያለው ግንኙነት ኢትዮፒካል ንክ
  በተሰኘ የሀገር ውስጥ የኤፍ.ኤም ሬዲዮ የመዝኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡

  ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄን ውድ አገራችንን በመላው የዓም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ከንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ መድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተገብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ የኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡ በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት ያቋረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፤ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ እና ሀገር ወዳድነት የጎደለው አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎድፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡

  ከዚህ በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችን እያረጋገጥን ከዚህ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸው ሰላማዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነት ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡›› ቢቀር ምን ይቀርበታል? ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከኮካ ኮላ የቀረበለትን ጥያቄ በደስታ ተቀብሎ የዓለም ዋንጫውን የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ተቀርጿል፡፡ ታድያስ መጽሔት ከአሜሪካ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ሙዚቃው እንደማይለቀቅ ከተነገረ በኋላም ኮካ ለድምጻዊው ተገቢውን የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ የተቀረፀው ሙዚቃ ንብረትነቱ የኔ ብቻ ነው የሚለው ግዙፉ የለስላሳ መጠጥ ካምፓኒ ለጊዜው ዘፈኑ ባይለቀቅም ለድምፃዊው ግን ተገቢውን ነገር እናደርጋለን የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከተመለከትነው ቴዲ ሙዚቃው ባለመለቀቁ ምንም አይቀርበትም ማለት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ድምጻዊው ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የምትታወቅበትን ዕድል አጥታለች፡፡ ቴዲም ቢሆን የደከመበት ሙዚቃ ከስቱዲዮ አለመውጣቱ ምቾት ይነሳዋል፡፡ ለምን ብሎ መጠየቁም ተገቢ መሆኑን የብዙዎቹ አድናቂዎች ሀሳብ ነው፡፡

  ‹‹ሾላ በድፍን››
  ኮካ በዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ራሱን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ሙዚቃዎች ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ላይ ለተከናወነው የዓለም ዋንጫ ‹‹waving Flag›› በሚል ርዕስ ሶማሊያዊው ድምጻዊ ኬናንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ድምፃውያን አሰርቷል፡፡
  በወቅቱ ይህ ሙዚቃ ተወዳጅ እንደነበር ይታወሳል፡፡የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር አጋር የሆነው ኮካ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ሙዚቃ በራሱ ስቱዲዮ መቅረጽ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡ ሳምባ በሚባለው የብራዚሎች ባህላዊ የሙዚቃ ስልት የተሰራው ‹‹The World Is Our›› የተሰኘው ሙዚቃ በተለያዩ ሀገራት ሙዚቀኞችና በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ሙዚቃ ዋና አቀንቃኝ በትውልድ ብራዚላዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነው ዴቪድ ኮሬይ ሲሆን ካለፈው መስከረም ጀምሮ ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተዘዋውሮ ሙዚቃውን መድረክ ላይ ተጫውቷል፡፡
  በዲቪድ ኮሬይ በዋናነት የተሰራው ይህ የኮካ ኮላ ሙዚቃ በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን በተለያዩ ቋንቋዎች ተቀርጾ ለጆሮ በቅቷል፡፡ ከስቱዲዮ ያልወጣው የቴዲ አፍሮ ብቻ ነው፡፡ ለምን? እስካሁን መልስ የለውም፡፡ የኮካ ኮላ ሰዎች ከአትላንታ ሰጡት በተባለው መግለጫና ቴዲ አፍሮ በድረ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ሙዚቃው ስላለመለቀቁ እንጅ በምን ምክንያት እንደሆን አይጠቅሱም፡፡ ነገሩ ‹‹ሾላ በድፍን›› ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ነገር በፊት ሙዚቃው ያልተለቀቀው በምን ምክንያት ነው? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

  ‹ኮካ ሀገሪቷን ደፍሯል?› ቴዲ አፍሮ በርካታ አድናቂዎች ካሏቸው አትዮጵያዊያን የሙዚቃ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለኮካ ኮላ ሙዚቃ ሊሠራ ነው ተብሎ ሲነገር እንደ አንድ በሀገር ኩራት ተቆጥሮ በመገናኛ ብዙሀን ሲዘወርለት ነበር፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ተጠግቶ ከነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጋር ተነጻጽሮ ሲቀርብ ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የሚወክለው›› የሚል መንደርደሪያ ከስሙ በፊት መጠቀስ ጀምሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሙዚቃው አለመለቀቁ በዚያ ሁሉ ሙቀት ላይ በረዶ እንደመጨመር ነው፡፡ ለዚያምነው በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ኮካ ኮላ አትጠጡ›› የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ብቅ ማለታቸው፡፡ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ከተጋዘበና ሙዚቃው በስቱዲዮ ከተቀረጸ በኋላ እዚያው ታፍኖ መቅረቱ ‹‹ክብረ ነክ›› መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹ሀገር ተደፍራለች›› የሚሉ ሀሳቦች በስፋት እየተነሱ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ መንግስት እጁንእንዲያስገባ የጠየቁም ነበሩ፡፡ ጉዳዩ ግን የሁለት አካላት ስምምነት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሀገራዊ አጀንዳ ለመሆን ግን አይበቃም፡፡ ተራ የቢዝነስ ስምምነትና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ የውል መፍረስ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡

  ኮካ ኮላ እንደአንድ የንግድ ተቋም ከድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የስራ ስምምነት አድርጓል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ተፈጻሚ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ ቴዲ አፍሮ ህጋዊ ጥያቄ ማንሳት ይችላል፡፡ ይሄን ለማድረግም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡ እንዴት ተሠራ?ኮካ ኮላ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ መሪ ድምጻዊ አድርጎ የመረጠው ዴቪድ ኮሬይን ነው፡፡ ይህ ድምጻዊ ከተለያዩ ሀገራት ድምፃዊያን ጋር የየሀገራቱን ቋንቋ በመጠቀም በጋራ ሙዚቃውን ሰርቷል፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ድምጻውያን ጋር በዚያው ቁጥር ልክ አንዱን ሙዚቃ ደጋግሞ ተጫውቷል፡፡ ይሄን ዕድል ካገኙ ድምፃዊያን መካከል ቴዲ አፍሮ አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅጅ የሆነውን ሙዚቃ ዴቪድ ኮሬይና ቴዲ በጋራ ቀርፀዋል፡፡ ኮካ ኮላ በተለያዩ ሀገራት የሙዚቃ ስቱዲዮዎች አሉት፡፡ የቴዲ አፍሮና የሌሎች አፍሪካውያን ድምጻዊያን ሙዚቃ የተቀረፀው ናይሮቢ በሚኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ሲሆን ጉዳዩን የሚከታተለውና የሚያስፈጽመው ደግሞ ማንዳላ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያው ግን ሙዚቃውን ‹የውሀ ሽታ› አደረገው፡፡መጨረሻው ምን ይሆን?

  ለዚህ ጥያቴ ምላሽ መስጠት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሙዚቃው ከስቱዲዮ እንዳይወጣ የተደረገበትን ምክንያት አለማወቃችን ከግምት ያለፈ እንዳንናገር ያስገድደናል፡፡ኮካ ኮላ ትልቅ የንግድ ስም ነው፡፡ በሀገራችን በብዛት ከሚዘወተሩ የለስላሳ መጠጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ደግሞ ብዙ አድናቂዎች ካሏቸው የሙዚቃ ሰዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ኮካ ኮላ በገበያው ላይ የሚደርስበትን ተጽዕኖ በመፍራት ችግሩን እልባት ይሰጠዋል ብለን መገመት እንችል ይሆናል፡፡በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ፀረ ኮካ›› ዘመቻ የጀመሩ የቴዲ አድናቂዎች የካምፓኒውን ስም ሊጎዱ የሚችሉ ሀተታዎችንም ደጋግመው እያስነበቡ ነው፡፡ ኮካ ለጤና ጠንቅ የሆነ ንጥረ ነገሮች እንዳሉት በመግለጽና የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ያልተለቀቀው ካምፓኒው ለኢትዮጵያ ካለው ንቀት የተነሳ መሆኑን በመዘርዘር አድማ እየቀሰቀሱ ነው፡፡

  ይህን ስንመለከት ካምፓኒው በኢትዮጵያ ያለውን ተቀባይነት ላለማጣትና ስሙን ለመጠበቅ ሲል ‹የታፈነውን ሙዚቃ› ሊለቀው ይችላል፡፡

   

  Read more
 • ቴዲ አፍሮ ኮካ ኮላ ባለፈው ሳምንት ላወጣው መግለጫ የሰጠው ምላሽ

   

   

  አስከመጨረሻው የዓለም ዋንጫ መከፈቻ ዕለት የመጨረሻ ሴኮንድ ድረስ እንጠብቃለን፡፡

  ሰኔ ግንቦት 23 2006 አለአግባብ እንዳይለቀቅ በተደረገው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ አስመልክቶ ያለንን አቋም በመግልፅ መግለጫ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡
  ምንም እንኳን መግለጫውን በድረ ገፃችን ላይ አትመን ለማውጣት ከመወሰናችን በፊት ጉዳዩን በተመለከተ ለኮካ ኮላ እና ወኪሉ ለሆነው ማንዳላ ቲቪ አስቀድመው እንዲያውቁት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ ላለፉት በርካታ ወራቶች ተደጋግሞ ሳያቋርጥ የገጠመን በመሆኑ የሚያስደንቀን አልሆነም፡፡
  እኛን ባስደነቀን መልኩ “ታዲያስ መጋዚን” በተሰኘ ድረ ገፅ ላይ ባለፈው ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ኮካ ኮላ ያወጣውን መግለጫ ለመመልከት የቻልን ሲሆን ምንም እንኳን ይህው መግለጫ በቀጥታ ለእኛ ያልደረሰን ቢሆንም ለክቡራን አድናቂዎቻችን በመግለጫው ውስጥ የተካተቱት ጭብጦች ምንም ዓይነት የውል፣ የፍሬ ነገር እና የህግ መሰረት የሌላቸው መሆኑን ማብራራቱ እና መግለፁ አግባብነት ይኖረዋል ብለን አምነናል፡፡
  መግለጫው ቴዲ አፍሮ ከኮካ ኮላ ጋር እንዴት እና ለምን ግብ ግንኙነት እንዳደረገ እንደሚከተለው በማተት ይጀምራል፤ “ቴዲ አፍሮ አፍሪካ ባለው የኮካ ሰቱዲዬአችን የመጣው የኮካ ኮላ ቅጂ የሆነውን “ዓለም የኛ ነች” የተሰኘውን የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ ልዩ ዓይነት የሆነውን ኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ለማሰቀረፅ በታቀደ ግብ ነበር” ይላል መግለጫው፡፡
  ይሁን እንጂ መግለጫው ማን “እንዳመጣው” እና ምርጫውንም እንዳደረገ አያመለክትም ወይም አይገልፅም፡፡ በመግለጫችን ላይ እንዳብራራነው ለኮካ ፕሮጄክት ወደ እኛ በመቅረብ ምርጫውን በማድረግ ተነሳሽነቱን የወሰደው አቶ ምስክር ሙሉጌታ ከመሆኑ በተጨማሪ ይህው ስው ከኮክ ሰቱዲዮ ጋር በማገናኘት ከኮካኮላ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ሊሚትድ ወኪል ከሆነው ከማንዳላ ቲቪ ጋር ውል እንድንዋዋል አድርጓል፡፡
  ከአቶ ምስክር እና ከማንዳላ ቲቪ ጋር ኮካ ኮላ በቅደም ተከተል የአሰሪ እና ሰራተኛ እንዲሁም የወኪል እና የወካይ ግንኙነት ያለው ቢሆንም በመግለጫው ላይ አንዳችም ዓይነት ግንኙነት ስለመኖሩ ከማስተባበሉ አልፎ በመሄድ “ከቴዲ አፍሮ ጋር የተደረገው ውል ማንዳላ ሊሚትድ በተሰኘ እና መቀመጫው ናይሮቢ በሆነ አዘጋጅ ተቋም “በ3ኛ ወገን” በኩል የተፈፀመ ነው” በማለት በአፅንኦት ገልጾ ራሱን ከነበረው ትስስር ነጥሏል፡፡
  3ኛ ወገን የሚለው ቃል …..የስምምነት ወይም የግብይት…. ወገን ያልሆነ እና አልፎ አልፎ ከስምምነቱ ወይም ከግብይቱ ውጪ የሆነ ወገን ተብሎ ይገለፃል፡፡ እንደ ኮካ ኮላ መግለጫ ከሆነ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የኮካ ኮላ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ምስክር ሙሉጌታ እና ለኮካ ኮላ በኮካ ስቱዲዮው በኩል ሙዚቃ ነክ ንብረቶችን ለማዘጋጀትና ለማስተዋወቅ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያቀርብለት ወኪሉ ማንዳላ ቲቪ ኮካ ኮላ ከአደረገው ስምምነት እና ግብይት እንዲሁም በመግለጫው ላይ “የኮካ ሰቱዲዬአችን” በሚል ፍንትው ባለ አገላለፁ ካመለከተው ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸው ባይታወሮች ናቸው፡፡
  አቶ ምስክር እንደ ተቀጣሪ ሰራተኝነታቸው እና ማንደላ ቲቪም እንደ ወኪልነቱ ልዩ ልዩ ሙዚቃ ነክ ንብረት አገልግሎቶች ለማከናወን በመዋዋል በማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ኮካ ኮላ ምትክ እና ፋንታ ህጋዊ ተግባራታቸውን ሲፈፅሙ ልክ ዋና መስሪያ ቤቱ አትላንታ ለሚገኘው እና መግለጫውን እንዳወጣው የኮካ ኮላ ተወካይ አንድ ዓይነት የሆነ የህግ ችሎታ/አቋም እና ውጤት አላቸው፡፡
  ይህ በራሱ ተቀጣሪ ሰራተኛ እና በወኪሉ መካከል ያለውን የፍሬ ነገር እና የህግ ትስስር ሙሉ ለሙሉ በመካድ ኮካ ኮላ ባወጣው መግለጫው ላይ “ሶስተኛ ወገን” የሚል ከቶም አግባብነት በሌለው ቃል ተክቶ ራሱን ከማናቸውም ግንኙነት ለማራቅ ምክሯል፡፡ ይህም ሁኔታ በቅዱስ መፅሐፍ ላይ ጲላጦስ የፈፀመውን ፈፅሞ “ከደሙ ንፁህ ነኝ” ያለውን ጥቅስ ያስታውሰናል፡፡
  ይህ ክብርን የሚያቃልል እና የሚነሳ መግለጫ የሰው ልጅን፣ የሁሉም አድናቂዎቻችንን እና የኮካ ኮላንም ደንበኞች ጭምር ዕውቀት፣ አእምሮ እና ግንዛቤ የሚገዳደር እና የሚፈታተን ነው፡፡ ይህም አድራጎቱ ቆሜለታለሁ ከሚለው የኩባኒያው የስነ ምግባር መርሆዎች ማለትም ከመልካም ስብእና፣ ታማኝነት፣ የህዝብ አመኔታ እና አሌኝታነት ጋር የሚፃረርም ነው፡፡
  በእርግጥ ኮካ ኮላ ከቴዲ አፍሮ ጋር ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት ከሌለው እንግዲያውስ በአጠቃላይ መግለጫውን ለማውጣትና ከሁሉም በላይ ደግሞ ቴዲ “ለአደረገው ጥረቱ ሙሉውን” የተከፈለው ስለመሆኑ እና “የተሰራው ሙዚቃ የማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ኮካኮላ ንብረት ሆኗል” በማለት አፅንኦት ሰጥቶ ለማረጋገጥ ለምን አሰፈለገው?”
  አሳዛኙ ነገር ላለፉት ወራቶች ከኮካ ኮላ እና ከማንዳላ ቲቪ ጋር ስናደርግ በነበረው የቃል እና የፁሁፍ ግንኙነቶች ተመሳሳይና አስደንጋጭ ጎጂ ተግባራቶችን ስንቀበልና ስናስተናገድ ቆይተናል፡፡ እነኚህ ድርጊቶች ከቅን ልቦና የመነጩ ወይም የዕውቀት ማነሰ ውጤት ናቸው የሚል ዕምነት የለንም፡፡ ይልቁንም ሆን ተብሎ የሚፈፀም ፍፁም ተቋማዊ የማናለብኘነት አድራጎት ነው፡፡
  ይህም ቢሆን ግን ራሱን በሚያከበር ኢትዮጵያዊ በሚመጥን ትዕግስት፣ ትህትና እና አክበሮት በጉጉት መለቀቁ እየተጠበቀ ያለውን ሙዚቃ ወይም ሊለቀቅ የማይችልበትን ምክኒያት አስከመጨረሻው የዓለም ዋንጫ መከፈቻ ዕለት የመጨረሻ ሴኮንድ ድረስ እንጠብቃለን፡፡

   

  Read more
 • በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

   

   

   

  በምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

  ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንም ቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

  በነገው እለት የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና በስፋት ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

   

  Read more
 • Reservations and Mass Graves in Minnesota and Oromia - amyvansteenwyk.tumblr.com

   

  As an ESL teacher who has worked with students from many different countries, I had reservations about focusing too much on one people’s struggles.  It felt unequal, unfair somehow.  

  I told myself, it’s okay.  Right now 100% of your students are East Africans.  Minnesotans know who Somali people are already.  Most have never heard of Oromo people.  They don’t know we have the largest population of Oromos outside of the Horn of Africa.  

  As a Minnesotan, I had reservations about focusing on anything so far away.  I am living on land that was stolen.  I am of settler descent.  My country was built on myths to justify genocide.  The fraction of what remains and who remains continues to be exploited and dismissed.

  I processed these reservations with trusted friends, with my husband, with activists, with East Africans.  Their counsel and wisdom was not to hold back.  One issue supports the other.  Both are indigenous peoples, colonized nations.  Both are even in Minnesota.  

  Turns out it was good advice.  Knowing more about what is going on in Oromia does inform my own understanding of the United States our ‘legacy’ here and in Africa.  Lately I hear a lot of news from far away - news that reminds me of Minnesota around the time it was just forming.  Like the trials and mass hangings of 38 Dakota men in 1862, ordered by President Lincoln.  Their physical remains did not rest in peace.  They were tossed in a shallow mass grave but just for a night.  The following day the bodies were dug up for use as medical cadavers. (http://usdakotawar.org/history/war-aftermath/trials-hanging)

  Today the news from Oromo friends and acquaintances is this:

   

  (via @LammiJar)

  • A mass grave has been uncovered in Ethiopia’s Oromia region during government-sponsored construction work at the site
  • The location where the discovery was made used to be a military facility where Oromo political prisoners were kept & many never came out.
  • The construction workers & local authorities tried to keep the discovery secret but information was leaked to the public leading to protesting.
  • Protesting has been going on for two days with people demanding that the construction be halted and asking for a thorough investigation.
  • Relatives of former prisoners who perished at the military facility are demanding that the remains be identified using scientific testing.
  • Prisoners who were at the military facility in the late 1990s say hundreds of Oromo political prisoners were killed at the site.

   

  The story is still unfolding. But it is unfolding in a climate where Oromo students are still being hunted down for conducting non-violent protests.  A climate where Oromo farmers still find their land squarely in the sights of foreign investors and a government eager to give away their land.  A climate where daily stories of torture and death wind their way from the prison cells and morgues to ears waiting years now for any news of life or death.  The marks of ethnocide and genocide against the Oromo people may be missing from most history books, but they permeate the oral history, and the collective memory of the people.

  The latest reports are of government forces shooting into the crowd.

  For info on recent protests in Oromia, Ethiopia:

  http://oromoprotests.com/

  http://www.tcdailyplanet.net/news/2014/06/06/community-voices-oromoprotests-perspective

  http://jenandjoshinethiopia.blogspot.com/ (esp. the three most recent posts) 

  Read more
 • በሐረር የተገኘ የጅምላ መቃብር ጥያቄ አስነሳ

   

  በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሐማሬሳ ቀበሌ ውስጥ ሰሞኑን በተገኘ የጅምላ መቃብር ምክንያት አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ጥያቄ ማንሳታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

  ሰሞኑን አካባቢው ለጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጆች ሼድ መሥሪያ ሲቆፈር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች አፅም መገኘቱን የጠቆሙት ምንጮች፣ የከተማው አስተዳደር ቁፋሮ እንዲቆም ቢያዝም፣ አንዳንድ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ መቆፈር እንዳለበትና በጅምላ የተቀበሩት ዜጎች ቁጥር መታወቅ እንዳለበት በመግለጽ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

  ቦታው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የሦስተኛው ክፍለ ጦር መቀመጫ እንደነበርና በደርግ ዘመነ መንግሥትም የጦር ካምፕ ሆኖ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

  ምንጮች እንደሚሉት በተለይ በደርግ ዘመነ መንግሥት በርካታ ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገድለው በጅምላ ተቀብረዋል፡፡ ኢሕአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ በተለያዩ አካባቢዎች በጅምላ የተቀበሩ ዜጎች አስከሬንን ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡ በሐረር ከተማም በዘመኑ በሰዎች ላይ ግድያ በጅምላና በተናጠል የተፈጸመ ቢሆንም፣ የተቀበሩበት ቦታ አለመታወቁና ጠቋሚ በመጥፋቱ እስካሁን ድረስ አስከሬኖች ሳይገኙ መቆየታቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

  ኢትዮጵያን ለ17 ዓመታት ሲመሩ የነበሩት ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምም፣ አሁን የጅምላ መቃብሩ በተገኘበት ቦታ ላይ የነበረው የሦስተኛው ክፍለ ጦር አባል እንደነበሩ የገለጹት ምንጮች፣ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ተቃውሞ ባደረጉ የኢትዮጵያ ወጣቶችና የወቅቱን ሥርዓት ተቃዋሚዎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ሁሉንም የአገሪቱን ክልሎች ያዳረሰ ለመሆኑ፣ የሐረሩ የጅምላ መቃብር መገኘት ማጠናከሪያ ማስረጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  በሐረር በተገኘው የጅምላ መቃብር ምክንያት በወቅቱ ለተሰው ዜጎች ማስታወሻ እንዲሆን ሐውልት ሊቆም እንደሚገባ አንዳንድ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩን መጠየቃቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

  በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ አካባቢ ተገኘ ስለተባለው የጅምላ መቃብርና አንዳንድ ነዋሪዎች አንስተዋል ስለተባለው ተቃውሞ ማብራሪያ እንዲሰጥ የክልሉ መስተዳደር ለመጠየቅ ቢሞከርም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ የጅምላ መቃብር መገኘቱ እውነት ነው፡፡ የተገኘውም ቦታውን ለጥቃቅንና ለአነስተኛ ተደራጆች ሼድ ሠርቶ ለመስጠት ቁፋሮ ሲደረግ መሆኑን አረጋግጠው፣ አንዳንድ የግል አጀንዳቸውን ለማራመድ ሰበብ የሚፈልጉ ግለሰቦች ሕዝቡን ከለላ አድርገው ለመንቀሳቀስ ሞክረዋል ብለዋል፡፡ ሕዝቡ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ አፍረው እንቅስቃሴያቸውን ማቆማቸውንም አስረድተዋል፡፡ ቁፋሮውም እንዲቆም ተደርጎ የክልሉ መንግሥት እየተነጋገረበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  Source: Ethiopian Reporter

   

   

  Read more
 • አብዲ ብያ:- አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የምንቃወምባቸዉ ምክንያቶች

   

   

  አብዲ ብያ

  የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የምንቃወመው፣

  1. ህገ መንግስቱን ስለሚጥስ፡፡ ኦሮሚያ በፌዴራል አወቃቀር ሉዓላዊ ክልል ነው፡፡ መሬቱንም የሚያስተዳድረው ክልሉ ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግስት ነው፡፡ ክልል በፌዳራል ስልጣን ውስጥ ጣልቃ አይገባም፣ ፌዴራል መንግስትም በክልል ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡

  2. አዲስ አበባ በኦሮሚያ መሃል ስለምትገኝ፣ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምን፣ የአካባቢ ብክለትን በሚመለከት ለኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል የሚለው ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ከፀደቀ 20 ዓመታት ቢያልፈውም ተፈጻሚ ሊሆን አልቻለም፡፡

  3. አሁን ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት መሬትን በመቀራመትና አርሶ አደሮችን ያለበቂ ካሳ ለመፈናቀል ተወዳዳሪ የማይገኝለት መንግስት በመሆኑ፣ የመሬት ስሪቱም መሬት የመንግስት ነው በሚል ታፔላ አርሶ አደሮችን ለማፈናቀል ወደ ኋላ ስለማይል ማስተር ፕላኑን መቃወም ተገቢ ነው፡፡ የኦሮሚያ መሬት እየተፈለገ ያለው ሁሉንም በእኩል በሚጠቅም ዘላቂ ልማት ሳይሆን በኪራይ ሰብሳቢነት መልክ የኢህአዴግ አባላትና ግብረ አባሮቹ መሬቱ ላይን ምንም ዕሴት ሳይጨምሩ የግል ሃብት ለማካበት አቋራጭ መንገድ ስለሆነ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡

  4. አዲስ አበባ/ፊንፊኔ ለኦሮሞ ህዝብ ታሪካዊ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ለኦሮሚያ ክልል ህጋዊ ዋና ከተማ መሆን ሲገባው፣ በተግባር ኦሮሚያ አዲስ አበባ ቢሮ ከፍቶ ከመቀመጡ ውጭ ምንም የባለቤትነት መብት የለውም፡፡ አማራ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ትግራይ ክልልና ሌሎቹም ብሄራዊ ክልሎች ዋና ከተማቸውን ለራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ኦሮሚያ የራሱን ዋና ከተማ ማስተዳደር ዕድል አላገኛም፡፡ በታሪክም ሆነ በጆኦግራፊ አቀማመጥ ከፊንፊኔ ውጭ ሌላ ከተማ ለኦሮሚያ ዋና ከተማነት አይታሰብም፡፡

  5. የ125 ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ ዕድገት ጋር በተያያዘ ነባሩ የኦሮሞ ህዝብ ከከተማው ሲፈናቀል እንጂ በከተማው ዕድገትና ልማት ውስጥ ሲታቀፍ አልተመለከትንም፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በመሳሪያ ጦርነት ሳይሆን በባህልና ቋንቋ ጦርነት ነው፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከምኒልክ ጊዜ ጀምሮ ስታበረታተ የነበረው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ባህልና ቋንቋን ነው፡፡ የባህልና ቋንቋ ተጽዕኖው ኦሮሞ ከአካባቢው እንዲሸሽ ያደርገዋል፡፡ ቋንቋና ባህል ማለት ድምጽ የሌለው መሳሪያ ማለት ነው፡፡ ቀላል ምሳሌ ልስጥህ፣ በአሁኑ ጊዜ አንድ ከጎጃም የመጠና አንድ ከሰበታ የመጠ የቀን ሰራተኛ በአንድ የግል ወይም የመንግስት ድርጅት አዲስ አበባ ውስጥ ተቀጥሮ በቀን ስራ ለመተዳደር የትኛው ዕድል ያለው ይመስለሃል? መቶ በመቶ የጎጃሙ ቀን ሰራተኛ የመቀጠር ዕድል ይኖረዋል፡፡ ምክንያቱም ባህልና ቋንቋ በሰው ልጅ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው፡፡ ስለዚህ በፊንፊኔ ከተማ ውስጥ በነበሩት ኦሮሞዎች ላይ የደረሰው የዘር ማጽዳት ዘመቻ በሌሎች ኦሮሚያ አካባቢ አንዲደገም ስለማንፈቅድ ማስተር ፕላኑን ለመቃወም ከበቂ በላይ ምክንያታዊ ነን፡፡

  Read more
 • Eutelsat says OMN of Minneapolis MN is the target of jamming

   

  Eutelsat also cites Ethiopia as sat-jammers

   

  By Chris Forrester

  A week ago it was Arabsat that was very publicly naming Ethiopia as the source of multiple jamming sessions to its broadcast channels. Now Eutelsat is piling on the pressure, also naming that Ethiopia is guilty of deliberate jamming, and of ramping up the signal jamming so that in 2013 it accounted for some 15 per cent of the operator’s problems.

  Eutelsat said the jamming is coming from northeast Ethiopia. Eutelsat says it is taking its complaints, via the French National Frequencies Agency, to the International Telecommunications Union, and to the Ethiopian government.

  The jamming is especially damaging in that it focuses not just on this or that channel – which would be bad enough – but on the entire transponder, and this affects dozens of perfectly innocent channels. Eutelsat officials strongly hint that the Ethiopean government is behind the problem, and that the interference is targeting the Oromia Media Network, of Minneapolis, USA, which provides a channel for the Oromia region of the country.

  Eutelsat says the jammers are using sophisticated high-powered antennas to disrupt programming on its satellites at 7 degrees West and 21 degrees East.

   

   

  Read more
 • VOA - ነቀምቴ ላይ አራት ከፍተኛ ሐኪሞች ታሥረዋል፤ አንድ ኮሪያዊ ተሰናብተዋል

   
  ዶ/ር አዳም ለማ፤ የቀዶ ሕክምና ሐኪም፣ ዶ/ር ኢሣያስ ብርሃኑና ዶ/ር በላይ ቤተማርያም የማኅፀንና የፅንስ ስፔሻሊስቶች፣ ዶ/ር ታመነ አበራ፤ ቀድሞ የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተርና አሁን ለስፔሻላይዜሽን የጥቁር አንበሣ ሬዚደንት ሐኪም፣ እንዲሁም ዶ/ር ሪም ጆንግ ሆ፤ ኮርያዊ የአጥንት ሐኪም፡፡
  ሁሉም በነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ አገልግለዋል፡፡

  ዛሬ ኮርያዊው ሐኪም ከሥራ ሲሠናበቱ አራቱ ኢትዮጵያዊያን ግን በቁጥጥር ሥር ውለው ነቀምቴ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
  ፈታሾች በዶ/ር አዳም ለማ ወላጆች ቤት - አዲስ አበባ

  የእነዚህ ለረዥም ዓመታት አገልግሎት ሰጥተዋል የሚባሉ ሐኪሞች ከሥራቸውና ከደመወዛቸው መታገድ፣ አልፎም መታሠር መነጋገሪያ እየሆነ ነው፡፡

  “ጥፋታቸው” የተባለው ምን ይሆን? በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችስ “ጥፋተኛ ናቸው” ብለው ያምናሉ?

  የተያያዘው ዘገባ የፖሊስን፣ የሆስፒታሉን አስተዳደር፣ የእሥረኞቹን ሐኪሞች ቤተሰቦችና ጠበቃ የሚሉትን ይዞ ዝርዝር መረጃ ይሰጥዎታል፡፡
  ያዳምጡት፡፡
   
   

   

  Read more
 • Doctor Belachew Tolera Yadeta arrested for Medical Malpractice

  A medical doctor who inflicted harm by negligence on a two months pregnant woman is arrested. The suspect Dr. Belachew Tolera Yadeta was accused by the prosecutor for medical malpractice. 

  The Federal First Instant Court’s menagesha area court that was seeing the case ruled him guilty in its June 3, 2014 session. The charge document shows that the doctor had inflicted physical harm on two months pregnant woman on October 23, 2014 at 11 A.M in the morning at the private clinic in the Gulelea subcity’s Kebele 09/15 of Addis. 

  Claiming that the fetus has defects and that it needs to be aborted, the Doctor, asking a payment of 987 Br inserted a metal instrument in the woman’s womb and pierced 3.2 centimeters of the woman’s womb and in the process damaging seventy centimeters of her small intestine where it has to be operated out later. Moreover, the malpractice has made 300 cc blood to be spilled into her abdomen. 

  The court that has been seeing the case for the past months ruled the doctor to be guilty and ordered for him to be in custody till a final verdict is passed on June 11, 2014. 

  - The Reporter

   

   

  Read more
 • ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ግርማ ብሩ – (እዶሳ አ ቱፋ)

   

  አቶ ግርማ ብሩ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግስት አምባሳደር።  በቅድሚያ ባህላዊዉና ወገናዊዉ ሰላምታዬ ይድረስዎት። በማስከተል ይህን ግልጽ  ደብዳቤ እንድጽፍሎት ያነሳሳኝ አልያም ያስገደደኝ በቅርቡ የድርጅቶትን የኢህ አዴግን ድል  ሀያ ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አትላንታ ከሚገኘዉ ጽናት ሬድዮ ጋይ ያደረጉት ቃለ መጠይቅ መሆኑን ልገልጽሎት እሻለሁ።http://www.ethiotube.net/video/31036/Tsenat-Radio-Atlanta–Solomon-Tekalign-interviews-Ambassador-Girma-Biru–May-2014

  ከቃለ መጠይቁ በእኔ አረዳድ እጅግ አስተዛዛቢ፣ አሳሳቢና አነጋጋሪ ጉዳዮችን  አድምጫለሁ። በእርግጥ ከኢሃዴጋዉያን አንደበት የተሻለ አልያም የተለዬ ጉዳይ መጠበቅ  ድርጅቱን አለማወቅ ነዉ። በመስማቴ የታዘብኳቸዉንና ያዘንኩባቸዉን ነጥቦች ከማንሳቴ አስቀድሜ እንደ አንድ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ስለ እርሶና ስለ ድርጅትዎ በተለይ ኦህዴድ ያለኝን እይታና ግንዛቤ ባጭሩ ላነሳልዎት እሻለሁ።

  በመጀመርያ ድርጅትዎ ኦህዴድ እርስዎና ባልደረብዎችዎ ፕሮግራሙን ሳትጽፉለት  ወይም ለመጻፍ ሳትታደሉ ሌሎች ወገኖች በሚመቻቸዉ ባሰቡትና በቀየሱት ተመስርቶ  በዚሁ ቅኝት ግዞት ተይዞ ወክለዋልሁ የሚለዉን የኦሮሞን ህዝብ የልብ ትርታ ለመስማት ሳይታደል እነሆ ሀያ አራት ኣመት መቁጠሩን እናንቴም ህዝቡም በወል እንረዳዋለን።

  ተመስርቶ በዓመቱ ለስልጣን የታደለዉ ይህ ድርጅት በበርካታ ወሳኝና ፈታኝ  በሆኑ ጉዳዮች ላይ እወክለዋለሁ ከሚለዉ ህዝብ ጎን አለመሆኑን እንድያዉም በተቃርኖ  የሚቆም መሆኑን በተግባር ያሳዬ ከሱ ሌላ እምነቶችም አቋሞችም ደካማና ጸረ ህዝብ  መሆናቸዉን ሊያሳምነን ስማስን የኖሬ ድርጅት ነዉ። ቆመለታለሁ የሚለዉ ህዝብ  እንዳዘነበትና ከልቡ እንዳራቀዉ ቆሞልናል የሚሉት ፈጣሪዎቹ ደግሞ ዉስጡን ለቄስ  ብሉም ላይ ላዩን ሲያወድሱትና ሲያሞግሱት ኖረናል።

  ይህን ስል ድርጅትዎን ስለማልደግፍ አልያም ሲለሚቃወም በጥላቻ መንፈስ ተነሳስቼ ሳይሆን እኔም እንደብዙዎች በቅርብ ርቀት ስልማዉቀዉ ያለዉም እዉነታ በጋሃድ የሚታይ በመሆኑ ከዚሁ በመነሳት ነዉ። ከአንደበታችሁ የሚንሰማቸዉ፣ ከተግባሮቻችሁ የሚናያቸዉ አልፎ ተርፎም ዘመን አልፎ ዘመን ስተካ የሚፈራረቁብን ግፍና መከራዎች ገሃድ ማስረጃዎች በመሆናቸዉ ነዉ።

  ምንም እንኳን የድርጅታችሁ ዓላማዉም አቅጣጫዉም ከኦሮሞ ህዝብ ዘላቂ ጥቅም አንጻር በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች ብኖሩትም ከፍሎቻችን በቅንነት ከሚናስባቸዉ እዉነታዎች ዉስጥ ጥቂቱ በዚህ ድርጅት ዉስጥ አንድ ቀን የህዝባቸዉ ጥልቅ ብሶት ተሰምቷቸዉ ድምጻቸዉን ከፍ አድርገዉ የሚያሰሙ፤ ገሃዱን እዉነታ በአደባባይ ወጥተዉ የሚመሰክሩ ግለሰቦች አይጠፉም የሚለዉ እሳቤ ነዉ። ይህን ስል ከእንግድህ በቃን አትፈለጉም ተብለዉ ከተጣሉ በሃላ የሚናገሩትን ሳይሆን ገና ወንበራቸዉ ላይ እያሉ ለእዉነት ስሉ ጥቅማቸዉንም የሚሰዉትን ለማለት ነዉ። በየዋህነት የዚህ አይነት እሳቤ ከሚያስቡት መካከል እኔም አንዱ ነኝ። በዚያ ደረጃ ከሚጠብቃቸዉም የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ እርስዎ ይሆናሉ ብዬም ባስብ የተወሰኑ መነሻዎች ስላሉኝ ነበር። እዉቀትዎም ሆነ የበርካታ ዓመታት ተሞክሮዎችዎ ለዚህ ያበቃዎታል ብዬም ነበር ይህን አስተሰሰብ ተሸክሜ የኖርኩት።

  በወገንዎ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተነጣጠረዉ መሰረተ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ ቅርጹንና ይዘቱን ይቀያይር እንጂ እያደር ከማገርሸት ሊመለስ አልቻለም። እኛም ወገንዎችዎ ብሶታችንን ስናሰማና ለመፍትሄም ስንጮህ እንደናንቴ አገላለጽ በሌላዉ ህዝብ ላይ ጥላቻ አድሮብን፣ ለራስ ብቻ ከማሰብ በአጭሩ በጠባብነት ሳይሆን ግፍና መከራዉ ስለበዛብን ሰሚ እናገኝ ይሆን ከምል መነሻ ነዉ። ታድያ አለመታደል ሆነና ፍትህ ጠማኝ ብሎ የሚጮሄዉ ሁሉ ጥይት እየጎረሰ ዳግም እንኳን ልጮህ ላይተነፍስ ጥሙን ሳይሆን እስትንፋሱን መቁረጥ ሆነ መልሳችሁ። ለዚህ ጽሁፍ ወደ አነሳሳኝ የሬድዮ ቃለ መጥይቅ በመመለስ ትዝብቶቼን ላቅርብሎት፥ ያልገቡኝንም ልጠይቆት።

  አንደኛ : ስለ ህገ መንግትዎ ዲሞክራሲያዊነት ሲያወድሱ « ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የልዩነት ሃሳብን በነፃነት ማቅረብን ይፈቅዳል። የሁከት ጎዳናን የመረጡት ወገኖች በነፃ ምርጫ የሚያሸንፉ መስሎ ያልታያቸዉ የህዝብን ዳኝነት ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ፤ ከሰለጠነዉ የዲሞክራሲ አሰራር ሃይልን አማራጭ አድርገዉ የሚወስዱ ናቸዉ » ስሉ እጅግ አስተዛዛቢና በእርሶ ደረጃ ካለ ሰዉ የማንጠብቀዉን ቃል ተናገሩ።

  ለምን ብሉ – እርግጥ ነዎት ህገ መንግስቱ ሃሳብን በነፃነት መግለፅን ይፈቅዳል። ነፃ ዉድድርንም ይፈቅዳል። በዚህ ረገድ እንከን የለዉም። ዳሩ ግን ህገ መንግስቱ ለራሱስ መች ነፃነት አገኘና ? ሃገሪቱ እየተመራች ሳይሆን እየተገዛች ያለችዉ በህገ መንግስቱ  ሳይሆን በድርጅታችሁ መመርያ ስለመሆኑ ምን የሚያከራክር ነጥብ አለዉ?

  « በምርጫ ዉድድር ለማሸነፍ እምነት ያጡ ወገኖች » ስሉስ ይህ ወቀሳ  ኢህአዴግን ነዉ ወይስ ለሎችን የሚገልፅ ይመስሎታል ? ከቶም በነፃ ዉድድር ማሸነፍ እንደማይችል በተግባር ያረጋገጠዉና የሃይል ጎዳናን የመረጠዉ ኢህአዴግ ስለ መሆኑ ከምርጫ ዘጠና ሰባት ኣላስተዋሉምን ? የኢትዮጲያ ህዝብ እኮ ድርጅታችሁን እንደማይሻ አስረግጦ ተናግሯል።

  « ተቃዋሚ ሃይሎች ከሰለጠነዉ መንገድ የሃይል ጎዳናን ይመርጣሉ » ስሉ ላለመሰልጠናችን መንስኤዉ ድርጅታችሁና እናንተዉ አመራሮቹ ስለመሆናችሁ ምን ጥያቄ አለዉ? ህዝቡን እኮ « ከዜላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃኔት » ብሎ ሞትን እንድጋፈጥ እያስገደዳችሁት ነዉ።

  የኦሮሞ ህዝብ ለፍትህ እንጂ ለስልጣን ስል እየሞቴ እንዳልሆነ ልቦናዎ አያጣዉም። ምክንያቱም ለአንድ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ስልጣን ለማግኘት እጅግ ቀላሉና ርካሹ መንገድ የኦህዴድ አባል መሆን እንደሆነ እናንተም ህዝቡም ጠንቅቀን ስለምናዉቀዉ ነዉ። ታድያ ፍትህንና እዉነትን ፍለጋ ካልሆነ ዉጣ ዉረድ የበዛበትን መንዋእትነት ጠያቂ የሆነዉን ሌላ መንገድ መምረጥ ለምን አስፈለገ?

  ስለ ስልጣን ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ልበልዎት። ኦህዴድ ሀያ ሶስት ዓመት በስልጣን ላይ የቆየዉ ህዝብ ወዶትና መርጦት አይደለም። ህዝብ የሚወደዉ ድርጅት ብሆን በርካታ አዳዲስ ፍሬዎችን በማፍራት አሮጌዉን በአዲስ ያረጀዉን በወጣት እዬተካ በተለሳለሰና ጠናማ በሆነ መልኩ ይጓዝ ነበር። ታድያ ድርጅታችሁ ለዚህ እዉነታ ባለመታደሉ አይደል እናንተዉ በጣት የሚትቆጠሩ አመራሮች ለዚህ ሁሉ ዜመን ከአንድ ወደ ሌላ ወንበር እየተሸጋገራችሁ ቀዳዳዉን ሁሉ ለመድፈን እዬማሰናችሁ በህዝቡ የብሶት ወላፈንም እየተፈጃችሁ ያላችሁት? ስለዚህ የስልጣን ጥሙ ከማን ዘንድ እንዳሌ ያዉቁታልና በሌላዉ ማላከኩ ይቁም እላለሁ።

  እባክ ዎትን እስኪ አሁንም አንድ እድል ነፃ የምርቻ መድረክ ይፍቀዱና የኢትዮጵያ ህዝብ ዳኝነቱን ይስጥ።

  ሁለተኛ : የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱትን ህዝባዊ የመብት ጥያቄ አስመልክተዉ በተናገሩት ላይ የሚከተሉትን አስተዛዛቢ ነጥቦች አንስተዋል። በሀገሪቱ ከሃያ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ወደ ት/ቤት መሄድ እንዳስቻላችሁ ከዚህም ዉስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እየሄዱ መሆናቸዉን በዉዳሴ ከገለፁ በሃላ « ተማሪዎቹ ለተቃዉሞ የተነሳሱት በተቃዋሚ ድርጅቶች ተቀስቅሰዉ ነዉ » ስሉ ተማሪዎቹ በራሳቸዉ አዉቀዉም ሆነ ተነሳሽነት ኖሮአቸዉ ይህን ጥያቄ እንደማያነሱ ቁጥራቸዉ በዛ እንጂ ለዚህ የሚሆን ብቃት የላቸዉም የምል እንደምታ ባለዉ መልኩ ገለፁአቸዉ። የኦሮሞ ተማሪዎች በወገኖቻቸዉ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና መከራ አይረዱም፤ ብረዱ በራሳቸዉ ተነሳሽነት ለመጠየቅ ብቁ አይደሉም ብለዉ ያስባሉን ? ይህ ከሆን የት/ፖሊሲዎትን ይመርምሩ። የነገዉ ሃገር ተረካቢ ዜጋም በምን ደረጃ ላይ እንዳሌ ያጢኑት።

  ከዚህም አያይዘዉ « ተቃዋሚ ሃይሎች በሸረቡት ሴራ ወጣቱን/ ተማሪዉን የእሳት እራት አድርገዉታል » ስሉ እጅግ አሳዛኝ አስፈሪና ኣሳሳቢ ነጥብ አንስተዋል። ተማሪዉ በራሱም ይሁን በለሎች ተታሎ ይህን ጥያቄ ይዞ ተነስቶ ከሆነ መልሳችሁ እሳት መሆኑ ነዉ ? የሃገሪቱ ዘጎችስ ተቃዉሞአቸዉን ለማሰማት ልዩነታቸዉን ለመግለፅ ብሻቸዉ እሳቱን እንደት ይቀርቡታል ? ከእሳቱ ለመታደግስ ከዘግነት በተጨማሪ ምን ዋስትና ማግኘት ያስፈልግ ይሆን ? መልሱን ለእርሶና ለድርጅትዎ።

  ሶስተኛ : በደረሰዉ የህይወት መጥፋት መንግስትዎ እንደሚያዝን የገለፁበት ጉዳይ ነዉ። መንግስትዎ ስለ ማዘኑ እርግጠኛ ነዎት? መንግስት ስለማዘኑ እስካሁን ለምን ይፋ አልተደረገም? በቀጣይ ላለመገደሉስ ምን ዋስትና አለዉ ዜጋዉ? ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌ፣ በአፋር ወዘተ ለተፈፀሙት የጅምላ ግድያዎች መንግስትዎ በየትኛዉ ተፀፅቷል ? ለመሆኑ የትኛዉንስ በገለልተኛ ወገን እንድጣራ ፈቅዷል ? ዳሩ ግን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወድህ እያዬነዉና እየተማርን ያለነዉ ህዝብ ሞትን በመፍራት መብቱን ከመጠየቅ እንደማይቆጥብና ይህንንም በተግባር እያሳዬ መሆኑን ነዉ። ህዝቡም ለመብቱ ፅኑ መሆኑን ገዢዉ አካልም እሳቱን ከማቀጣጠል ሌላ አማራጭ እያጣ መምጣቱን ነዉ እዉነታዉ እያሳየን ያለዉ።

  አራተኛ : ያረቀቃችሁት የአዲሱ ማስተር ፕላን ጉዳይ ነዉ። « ተማሪዎቹ በቂ እዉቀትና ግንዛቤ ሳይኖራቸዉ ድብቅ ዓላማ ባላቸዉ ወገኖች ተታለዉ ነዉ ጥያቄ ይዘዉ የተነሱት። ፕላኑ ገና በረቂቅ ደረጃ ነዉ ያለዉ። ገና ለህዝብ ቀርቦ ዉይይት ይደረግበታል። ስልዚህ የሚያሰጋና ለቅሬታ የሚያደርስ ነገር ኣልነበረበትም »። ስሉ የተማሪዉን ጥያቄና የህዝቡን ቅሬታ አጣጥለዉታ።

  አዲሱን ማስተር ፕላን የኦሮሞ ህዝብ በሩቁ ብፈራው እዉኔት አለዉ። ምክንያቱም በየትኛዉም ጉዳይ ላይ ህዝብን ማማከር፤ የዝብን ስሜት ማዳመጥ የሚባል ነገር በልምዳችሁ ዉስጥ ስልማይታወቅ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል ብሎ ነዉ ህዝቡ ያወያዩናል ብሎ የሚጠብቃችሁ? ከናንቴ ለላ አቋም ያላቸዉን ድርጅቶች በሽብርተኝነት እዬፈረጃችሁ ከሃገር ስታሳድዱ፤ የመረዳጃ ተቋሞቻችንን በአዋጅ እያፈረሳችሁ ንብረታቸዉን ስትወርሱ፤ ህዝቡን በገፍ እንድ ናዚዉ ስርዓት ወዴ እስር ስታግዙት፤ የፍንፊኔ /አዲስ አበባ/ን ክልል በመቶ ሺህ የሚቆጠር አርሶ አደር ከቤት ንብረቱ አፈናቅላችሁ በድህነት ተጎሳቁሎ ተከብሮ በኖረበት መንደሩ በበረንዳ ወድቆ በረሃብ እንድሞት ስትፈርዱበት፤ ከቀየዉ ላለመፈናቀል የሚያሰማዉ ጩሄት ሰሚ እንዳያገኝ በቀላጤ አዋጃችሁ የፍርድ ከለላ ስትነሱት፤ ፊንፊኔ የኦሮሚያ እምብርትነቷን ነፍጋችሁ መስተዳድሩን በህዝቡ ጩሄትና ደም ላይ እየተረማመዳችሁ አዉጥታችሁ ወደ ሌላ ስትሰዱበት፤ ስለ ህዝቡ የሚቆረቆሩትንና የሚናገሩትን በፈጠራ ወንጀል በየማጎርያችሁ ስታሰቃዩአቸዉ ህዝቡ በምን ያምናችሃል?

  ሃያኛ ዓመት ልደቱን ሊያከብር በደረሰዉ ህገ መንግስት አንቀፅ 49-5 የኦሮሚያ ክልል በፊንፍኔ ላይ የሚኖረዉ ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል ይላል። የዚህን አንቀፅ አፈፃፀም አዋጅ ላለማዉጣት ታቅባችሁ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም በግልፅ ወደ ጎን በመተዉ ዛሬ ለግዛት ማስፋፋት ልዩ ራእይ ሰንቃችሁ መነሳታችሁ በራሱ የትልቅ አደጋ ምልክት ነዉ።

  ለነገሩ ከከተማዉ ዉጪ ባሉት አዋሳኝ ወረዳዎች የሚገኙ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ከማሳቸዉ እዬተፈናቀሉ እንደሆነ የቀሩትም በቁጥጥር አልባዉ የልማት ተልእኮ ወንዞቻቸዉና ኩሬዎቻቸዉ በመርዛማ ንጥሬ ነገሮች እዬተመረዙ እንስሶቻቸዉ በገፍ እያለቁባቸዉ እንደሆነ እርሶም ጠንቅቀዉ ያዉቁታል። ህዝቦቹም እጅግ በከፋ የተስፋ መቁረጥና የከለላ ማጣት አደጋ ላይ እንዳሉ እንኳን ለእርሶና ለእኛ ለወገኖቻቸዉ ሌላዉ ዓለም የአደጋዉን አሳሳቢነት ተገንዝቦ እየጮሄላቸዉ ነዉ ያለዉ።

  ከተሞቹ አይደጉ፤ አካባቢዉ አይልማ ብሎ የተቃወመ አልያም በከንቱ የጮሄ የለም። እድገቱም፣ ልማቱም የኦሮሞን ህዝብ እዬበላና እያጠፋ አይሁን ነዉ። በፊንፍኔ የተፈፀመዉ ግፍ በሌላዉም አይደገም ነዉ። ይህ ተግባር የዘር ማጥፋት ወንጀል ስለሆነ ይቁም ነዉ። በዚህ መርሃግብር መሰረት የኦሮሞ ህዝብ መፈናቀሉና ለእልቂትም መዳረጉ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ እሴቱ ጭምር ነዉ እንድጠፋ እየተደረገ ያለዉ። ይህ ደግሞ ዓላማዉ ግልፅ ያልሆነ ለህልዉናችን የሚያሰጋን አደጋ ነዉ። በዚህ ተግባር ዉስጥ ድርጅትዎ ምናልባት ለመወሰን ባይታደልም ለማስፈፀሙ ግን ግንባር ቀደም ነዉና የአደጋዉን ክፋት ተገንዝቦ፤ የህዝቡን የልብ ትርታ ሰምቶ አካሄዱን ያርም ነዉ። ከቻለም የከዚህ ቀደም ተግባራቱን መለስ ብሎ ይመርምር ነዉ።

  አንድ ህዝብ ከተፈጥሮአዊ አካባቢዉ እየተፈናቀለ በሄደ ቁጥር ቋንቋዉ፣ ባህሉ፤ ቁሳዊ እሴቶቹ ወዜተ ከመጥፋታቸዉ ባሻገር ሰብዓዊ ክብሩን ሳይቀር እየተገፈፈ ይሄዳል። ይህ ደግሞ ምንም ፍልስፍናም አይደለም። በወል በተግባር እያየነዉ ያለነዉ ጉዳይ ነዉና።

  አምስተኛ : በንግግርዎ መግቢያ ላይ ኦሮሚያ ዉስጥ ተቃዉሞ በተቀሰቀሰበት ወቅት በቦታዉ ስላልነበሩ ዕዉነታዉን በትክክል መግለፅም ሆነ ዳኝነት መስጠት እንደሚከብድዎት በመናገር ዕዉነታነት ያለዉ አቀራረብ ቀረቡ። ከደቂቃዎች ንግግር ብሃላ ግን « የፀትታ ሃይላችን በከፍተኛ ደረጃ ከታጠቀ ሃይል ጋር ነዉ የተጋፈጠዉ » ስሉ ባልነበሩበትና ባላዩት ጉዳይ ምስክርነትዎን ከመስተትዎ በተጨማሪ « እንዲያዉም የሰዉ ህይወት የጠፋዉ በወድያ በኩል በተተኮሰ ጥይት ነዉ » ስሉ ፍርደ ገምድል የሆነ ዳኝነት ሰጡ። ይህ አገላለፅ በሃገሪቱ የዳኝነት ስርዓት በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያሳይ ግልፅ ማስረጃ ነዉ። እርሶ አሜሪካ ተቀምጠዉ መበየን ከቻሉ ሃገር ቤት ያሉት ባለስልጣናት ደግሞ አይተናል ሰምተናል እያሉ ምን ይሉ ይሆን?

  እዚህም ላይ አንድ ትዝብቴን ላነሳሎት እሻለሁ። የአብዛኛዉ ህዝብ እንደሚሆንም ገምታለሁ። የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሌሎች ሁሉ በማስተር ፕላኑ ላይ ያላቸዉን ቅሬታ በመግለፅ ያላቸዉን ጥያቄዎች መንግስታዊ ምላሽ እንድያገኙ ለሚመለከተዉ አካል አቅርበዉ በተመለሱ በማግስቱ ፍፁም ባልተጠበቀ ሁኔታ በከተማዉ ዉስጥ ለተቀሰቀሰዉ ሁከት የመንግስት እጅ ስለ መኖሩ የሚያጠራጥር  አይደለም። ምክንያቱም የተፈፀመዉ የዘረፋና የንብረት ማዉደም ተግባር ከቶም ከተማሪዎቹ ጥያቄም ሆነ ከተቃዉሞአቸዉ ጋር ጉድኝት የለለዉ ሆን ተብሎ የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን ለመወንጀል የተቀነባበረ፤ በማግስቱም የተለመደዉ ኢህአዴጋዊዉ የተለቪዥን ድራማ የተሰራለት፤ አምቦን በመምታት ሌላዉን ማስተኛት የሚል ይዞታ  የታዬበት በመሆኑ ነዉ። ይህ ደግሞ ምንም አዲስ ክስተት አይደለም። ህዝቡ  የለመደዉና ምናልባትም ከእያንዳንዱ ክስተት ጀርባ የሚጠብቀዉ ነዉ። ህዝቡ ካካበተዉ  ተመክሮ አንድ ክስተት ስፈፀም ሁለተኛዉን በእርግጠኝነት የመናገር ሶስተኛዉን ደግሞ መገመት በሚችልበት ደረጃ ነዉ ያለዉ።

  ለመሆኑ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖበታል በተባለለት ሀገር በከፍተኛ ደረጃ የታጠቄ ሃይል አምቦ ድረስ ከዬት መጣ? የዚህ መሰል ችግር ካሌ ምን ያክል ህዝቡ ከመንግስት ጎን መሆኑን መመርመር ያሻል።

  በመጨረሻም ከአንድ መንግስት ሀላፊነቶች አንዱ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል በዜጎች መካከል እንድኖር ማስቻል ነዉ ። ይህ ግን ከአንዱ ነጥቆና አደህይቶ፤ በተልይ በተፈጥሮ ከተቆራኘበት መሬቱ አፈናቅሎና ህልዉናዉን አጥፍቶ ልሆን አይገባዉም ባይ ነኝ። የህዝብን ጥያቄና ብሶት መስማት ለህዝቡም ለራስም ክብር ነዉ። « ይህ የጥቂቶች ጥያቄ ነዉ ፤ የስልጣን ጥመኞች ድብቅ ሴራ ነዉ » እያሉ ዕዉነትን ማድበስበሱ ችግርን እንጂ መፍትሄን አይወልድምና።

  Contact : [email protected]

   

  Read more
 • ስለ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያዊው ቅጂ ሙዚቃ ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ፡ “ጉዞው ይቀጥላል!”

   

   

  ስለ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ የተሰጠ መግለጫ

  ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም “ቴዲ አፍሮ” ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ በሚጎርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ስደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ የግንኙነቱን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባን እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው ቴዲ ከኮካ ጋር ያለውን ግንኙነት ኢትዮፒካ ሊንክ በተሰኘ የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡

  ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄውን ውድ አገራችንን በመላው የአለም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለምአቀፍ የስፖርት ክንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለምናደርገው ጥረት ሲባል በፍፁም ቅን ልቦና ተቀብለናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሚለቀቅበት ወቅት የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ የቴዲ አፍሮን ዓለም አቀፍ እውቅና እና ዝና፣ የሥነ ጥበብ ገፅታ እና ስብዕና የበለጠ ከፍ እንደሚያደርገው እና እንደሚያጠናክረው በሚገባ እንገነዘባለን፡፡

  ለታፈረችው አገራችን፣በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚገኙት ለውድ አድናቂዎቻችንና ለሰው ልጆች ሁሉ ባለን የማይታጠፍ ታማኝነት በኮካ ፕሮጄክት ተሳታፊ መሆናችን ትክክለኛ እና አግባብነት የነበረው ውሳኔ ነው፡፡ በዚህም ምክኒያት የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ የቴሌቪዥን ቀረፃው የተሻለ ውጤታማነት ይኖረው ዘንድ ቴዲ አፍሮ በበኩሉ አቅሙ የቻለውን ያህል ጊዜውን፣ጉልበቱን እና ስነ ጥበባዊ ክህሎቱን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥረት አድርጓል፡፡ በኮካ ሰቱዲዮ ፕሮጄክት ተሳታፊ የመሆኑ ዋነኛው ፋይዳ አለም አቀፍ ተዋቂነት ባለው ብራንድ በመጠቀም የኢትዮጵያን አዎንታዊ ገፅታ ለማጉላት የመላውን ዓለም ህዝብ ትኩረት ለመሳብ የሚያስችል ከባድ ያለ ተልዕኮ ለመወጣት እንጂ የንግድ ዕቃ በማስተዋወቅ ለሚያስገኘው እምብዛም ያልሆነ ጥቅም አልነበረም፡፡

  በመሆኑም ሙዚቃ ነክ ንብረቶችን በማዘጋጀት እና በማሰራጨት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለኮካ ኮላ የማዕከላዊ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ለመስጠት ወኪል የሆነው ማንዳላ ቲቪ የዝግጅት ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ዴቪድ ሣንደር፣ በኮክ ስቱዲዮ የተሰራው የቴዲ አፍሮ ስራ በሚያስደንቅ እና በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን የሚገልፀውን ስሜት ቀስቃሽ እና አጓጊ ዜና እና ብስራት የተቀበልነው በከፍተኛ ክብር፣ ኩራት እና እርካታ ሲሆን ይህው ሰው ከዚያም አልፎ “የአለም ዋንጫ ቪዲዮው ተዘጋጅቶና ተከፋፍሎ ምናልባት በጥር ወር በኮካ ኮላ ይለቀቃል” በማለት አረጋግጦልናል፡፡ ከሥራው መጠናቀቅ በኋላ በውጤቱ የተደሰቱት የቴሌቪዢን አዘጋጆች እዚያው ላይ ቴዲ አፍሮ በአንድ የኮካ የሙዚቃ አልበም ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ያቀረቡለትን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል በሥራው የተሳተፈ ሲሆን ይህም ስራ “የአዲስ አመት ክንውን” ሆኖ ባለፈው “ታህሳስ 22 ቀን በአራት አገሮች ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እንዲጫወት ተደርጓል፡፡”

  ከበርካታ ቀናት በኋላ፣ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ መለቀቅ በጉጉት በምንጠባበቅበት ወቅት አቶ ምስክር የተጠናቀቀውን የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ እንድንመለከተው የጋበዘን ሲሆን በአርቲስቱ ሥራም እንደ ቴሌቪዢን አዘጋጆች ሁላችንም በጣም ደስተኛ ነበርን፡፡ ከጥቂት ጊዜ ባኃላ ግን ከባዶ መነሻነት አስደናቂ መጠማዘዝ ያሳየው አቶ ምስክር ፍርሐት በሞላው ድባብ በተጠናቀቀው ሥራ ላይ የነበረው የቴዲ አፍሮ ተሳትፎ እና ሽፋን “ዝናውን የሚመጥን አይደለም” በሚል የተጠናቀቀው ሙዚቃ እንዳይለቀቅ ድጋፍ እና ተቀባይነት ለማግኘት የሙከራ ጥረት አደረገ፡፡ ይህንን አቋሙን እንቀበልለት ዘንድ ለማሳመን ያደረጋቸው ሁሉም ጉዞዎች እና ኩነቶች በጉዳዩ ላይ “የቴሌኮንፈረንስ” እንዲካሄድ በመጠየቅ ከመታጀቡ በተጨማሪ በእርሱ አስተሳሰብ “ውድቀት” ሊሆን ስለሚችለውና የያዘውን አቋም አስመልክቶ ቴዲ አፍሮ ለህዝብ እንዳይገልፅበት እንድንታቀብ አስከማስፈራራት የደረሰ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ከመነሻው ጀምሮ በኮክ ፕሮጄክት ተሳታፊ እንዳልነበረ እና የኮካ ወኪል ከሆነው ከማንዳላ ቲቪ ጋር እንድንገናኝ ለማድረግ እና እኛን ለማሳመን እንዳልተሳተፈ ሁሉ አቶ ምስክር ከስራው ጋር በተያያዘ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረን ግንኙነት በማስተባበል ራሱን በማራቅ ብሔራዊ እና ህዝባዊ ሃላፊነቶችን በተጋረደ ጠባብ የግል ጥቅም ለመለወጥ በፈፀመው አሳፋሪ፣ አገር ወዳድነት በሌለው የፈሪ ተግባሩ ኃላፊነትን ላለመሸከም በማሰብ ራሱን የማሸሽ እንቅስቃሴ አደርጓል፡፡

  በኮካ ሰቱዲዮ የዝግጅት ሥራ አስኪያጅ በኩል ከቴክኒክ አኳያ የተጠናቀቀው ስራ የላቀ ጥራት እንዳለው በተደጋጋሚ ተረጋግጦልናል፡፡ በመሆኑም የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃን ይዞ በማቆየት እንዳይከፋፈል እና እንዳይለቀቅ የተደረገበት ምክኒያት እና የመጨረሻ ውሳኔ ከአርቲስቱ ወይም ከሥራ አስኪያጁ ጋር ምንም ውይይት ሳይደረግ እና ሳያውቁት በአቶ ምስክር ሙሉጌታ እና በኮካ ወኪል ማንዳላ ቲቪ የተሰጠ የጋራ ውሳኔ ነው፡፡

  የተጠናቀቀው ሥራ ተሰራጭቶ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም፣ ከወኪሉ በመጨረሻ ላይ ያገኘነው ምላሽ ግን “በዚህ ደረጃ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ለጊዜው አንለቀውም” በሚል የተገለፀልን ከመሆኑ በላይ በእኛ ዘንድ የተፈጠረውን ሃያል ቁጣ በማባበል ለማቀዝቀዝ የሚሞክር እና ሥራውን ወደፊት ሊለቁት እንደሚችሉ ለማሳመን የሚጥር ማታለያ እና ለምንወዳት አገራችን፣ ለሁሉም ራሱን ለሚያከብር ኢትዮጵያዊ፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአገር ውስጥ እና የውጪ አድናቂዎች እና ለአርቲስቱ በቁስል ላይ እንጨት የመስደድ ያህል ሆኖብናል፡፡

  በበኩላችን በተጠናቀቀው ሥራ ላይ ስለተወሰደው ተገማችነት ላልነበረው የዱብዳ እርምጃ ለአቅረብነው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው በርካታ ጥረት ትኩርት የተነፈገው ወይንም ከነጭራሹ ችላ ከመባሉ ውጪ ምላሽ የተሰጠውም ትዕግስታችን ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡

  በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ ለመድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተግብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ ይኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡

  በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት የቆረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፣ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ፣ እና አገር ወዳድነት የጎደለውን አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎደፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡

  ከዚህም በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችንን እያረጋገጥን ከዚሁ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸውን ሰላማዊ እርምጃዎችንም በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነትን ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ ጉዞዉ ይቀጥላል!

  Read more
 • Coca-Cola Issues Statement Regarding Teddy Afro


  New York (TADIAS) — The Coca-Cola Company, headquartered in Atlanta, responded to queries regarding the unreleased, Ethiopian version of Coke’s FIFA World Cup song performed by Teddy Afro. Coca Cola confirmed that Teddy’s contract was handled by a third party, Mandala Limited, a Kenyan production company based in Nairobi.

  “Teddy Afro was brought into our Coke Studio in Africa to record a version of the Coca-Cola FIFA World Cup song, ‘The World is Ours’ with the goal of capturing the unique genre of Ethiopian music,” a representative of The Coca-Cola Company said in an email to Tadias Magazine. “The contract with Teddy Afro was executed by a 3rd party, Mandala Limited, a production House based Nairobi and Teddy Afro was compensated in full for his efforts.”

  Per the contract, Coca-Cola said, “following recording the produced track become the property of Coca-Cola CEWA to be used at the Company’s discretion. The song has not been released and there are no plans for release at this time.”

  The company noted that currently there are 32 local versions of the track that have been released worldwide, but it remains unclear why Coca-Cola chose not to release the Ethiopian version.

  - See more at: http://www.tadias.com/06/07/2014/coca-cola-issues-statement-regarding-teddy-afros-version-of-fifa-world-cup-song/#sthash.cET5eOsu.dpuf

   

   

   

  Read more