የኦሮሞ ህዝብ በፍፁም መሳሳት ያሌለባቸው ሶስት ቁልፍ ጉዳዮች!

1ኛ፣ የኦሮሞ ህዝብ ትግል በምንም ዓይነት ሁኔታ ሳላማዊ የትግል መስመሩን ለቆ ወደ ግጭትና የትጥቅ ትግል እንዳይቀየር ህዝቡ በተላይም ወጣቱ ሰላማዊ የትግል መስመሩን በትጋት መጠበቅ አለበት።ህዝባችን ራሱንና ንብረቱን ከጥቃት የመከላከል ራስን የመከላከል መብቱ ምን ጊዜም የተጠበቀ ነው። ይህንንም በግልፅ በህጋዊ መንገድ በራሱና ከውስጡ በወጡት ፓሊስና ወታደር ማድረግ ይችላል።በአገር ውስጥ ያለውን የኦሮሞ ወታደርና ፓሊስ የራሱ ማድረግ እየቻለ ልጆቹን ወደ ውጭና የማይታመኑ ጎረቤት አገሮች ልኮ በውትድርና ያሰለጥኑልኛል ብሎ ማሰብ የለበትም። የትግሬ ታጣቂ ለትግራይ ህዝብ የሚሞት ከሆነ የኦሮሞ ወይም የአማራ ወታደር ለህዝባቸው ክብርና ጥቅም የማይሞቱበት ሁኔታ በፍፁም ሊኖር አይችልም። ቢበዛግንዛቤውን ለማስረፅ ትንሽ ስራ ይጠይቅ ይሆናል። ነገር ግን ህወሃትና ከህወሃት ጋር የሚሰሩ ነፈሰ ገዳዮችና ሌቦች የህዝባችን ትግል ሰላማዊ መልኩን ትቶ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲቀይር እየሰሩ ነው። ይህን የሚያደርጉትም ትግሉ ከኦሮሞ እጅ ወጥቶ ውጭ ባሉ ሌቦች እጅ እንዲገባና ያለፈው 27 ዓመት አዙሪት ህዝባችን ላይ እንዲመለስ ለማድረግ ነው።ይህ የኦሮሞ ፓለቲካ ዳግም ከአገር እንዲሰደድና በውጭ በጥገኝነት እንዲኖርና የሌሎች ኃይሎች መጫወቻ እንዲሆን ያደርጋል። ስለዚህ የህዝባችን ትግል ሰላማዊ መልኩን እንዳይቀይር ሁላችንም መጠበቅ አለብን።

2ኛ፣ የተነቃነቀው ህወሃት ተነቅሎ ካልጠፋ የኦሮሞ ህዝብ በፍፁም በሰላም መኖር አይችልም።ስለዚህ ህወሃት ሁለተኛ ተመልሶ እንዳያቆጠቁጥ መቁረጥ ሳይሆን ከስሩ ተነቅሎ መጥፋት ያለበት ድርጅት መሆኑን የኦሮሞ ህዝብ ግልፅ ውሳኔ ላይ መድረስ አለበት። ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ መሬታቸውንና ንብረታቸውን ለመዝረፍ የራሱን ታጠቂዎች አሰማርቶ ያፈናቀለ ሌባና ነፈሰ ገዳይ ቡድን በህዝባችን ላይ መንግስት መሆን አይችልም። በሞያሌ 50 ሺህ ህዝብ ያፈናቀለ የትግራይ ታጣቂ ቡድን በህዝባች መከከል በፍፁም መኖር የለበትም። እንደ ታዬ ደንደኣ ዓይነት ለሰው ልጆች እኩልነት(የትግራዩ ሌባ ህወሃትን ጨምሮ) የሚታገሉ ቅንና እውነተኛ ሰዎችን ያሰረ ቡድን ከየትኛውም ኦሮሞ ህዝብ መሪና እውነተኛ ኦሮሞ ጋር አብሮ መኖርና መስራት አይችልም። ስለዚህ ህወሃትን ከኦሮሚያ መንቀል ብቻ ሳይሆን ከህወሃት ጋር የሚሰራና የሚታባበር እንኳን ሰው የኦሮሞ ውሻ እንኳን እንደይኖር ግልፅ አቃም መያዝ አለበት።

3ኛ፣ የነለማ መገርሳና የዶ/ር አብይ ቡድን በኢህዲግ ውስጥ ስልጣን ይዘው የሥረዓት ለውጥ የሚያመጡበት ሁኔታዎች ከሉ የኦሮሞ ህዝብ ሙሉ ድጋፉን ሊሰጣቸው ይገባል። ያ ሳይሆን ቀርቶ ህወሃት እነርሱን በማደናቀፍ ወይም እነርሱን ከፊቱ አድርጎ ዕድሜ መግዠና እንደ ጊዜ ማራዘሚያ ለመጠቀም ቢሞክር የኦሮሞ ህዝብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝቦች አስተባብሮ ይህን ሰው በላ ስራዓት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ትግሉን አፋፍሞ ለመቀጠል መዘጋጀት አለበት።

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles