To Abebe Bogale and ESAT - ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ ተከዜን ሳይሻገሩ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ይቁም!!

ድሮም አልነበሩም አሁንም የሉም!! መጋቢት 3/2009

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የወያኔ ኢሃዴግ አንባገነንነትንና ገዳይነት በመቃወም በሁሉም አቅጣጫ ትንቅንቅ በማድረግ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ቤቴን ፣ንብረቴን ፣ቤተሰቤን ሳይል ከሁሉ በፊት ኢትዮጵያን በማስቀደም በዱር በገደሉ ሕይወቱን መስዋዕት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ከወዳጆቻችን አልፎ ጠላቶቻችን ምስክሮች ናቸው።

ይህ የትግል ጉዞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል በሚል የተለያዩ አወንታዊ ተሞክሮዎችን በማድረግ ለለውጥ የሚያደርጉት ሂደቶች በጥቂት መሰሪና ብልጣብልጥ የትግሉ ተባዮች እንቅፋት እየሆኑበት ይገኛል።

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በኩል በተለያዩ ጊዜያት ያለውን ወቅታዊ ችግር ለማሳወቅ ለሕዝባችንና ደጋፊዎቻችን የተለያዩ መግለጫዎችን ማውጣታችን እሙን ነው።

ይሁን እንጂ የግንቦት 7 አመራር ነን የሚሉ የስልጣን እርከኖቻቸውን እንደ ሸሚዛቸው እየቀያየሩ በመልበስ የሚያስተላልፉት ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ የሃሰት ወሪያቸው ፣የትግሉን አቅጣጫ መሳትና የሕዝባችንን በሰበር ዜና መታለል ስንገነዘብ ልባችን ይደማል።

በተለያዩ ጊዜያት የግንቦት 7ቱ መሪ ፕሮፊሰር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነትና ሰራዊት ሳይኖራቸው አስተናጋጅ ሃገር የጫጉላ ጊዜያቸውን ጨርሰው በኣውሮፓና አሜሪካን ሃገራት ተመሽገው የተለመደና የተጠና ያልተጨበጠ ቅስቀሳቸውን ከኤርትራ እየተባለ በሚቀርብልን ዩቲዩብ ቪዲዮ እና በሚዲያቸው የሚያቀርቡት ንግግር የትግሉ እንቅፋት ብቻ ሳይሆን ለጠላታችን ወያኔ ጥሩ መረጃና በሃገር ወስጥ ለሚገኙት ተቃዋሚ ሃይላት የትግሉ ጋሪጣ ለመሆኑ የሚታዩትና የሚሰሙት ንግግሮች በቂ ማስረጃዎች ናቸው።

በቅርቡ የግንቦት ሰባቱ ምክትል ሊቀመንበርና በአዲሱ ሹመታቸው የሕዝብ ግንኙነት አቶ አበበ ቦጋለ አማካኝነት በራሳቸው ሚዲያ እና በህሌና ኢትዮጵያ ራዲዮ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አንዲት ሳንቲም፣አንዲት አረር፣አንዲት ሰባራ ጠመንጃ ሳያቀብሉ ወይም ሳይሰጡ ‘’ በሃገር ወስጥ የሚንቀሳቀሱትን እየረዳን ነው ያለነው’’ ከአርበኛ ጎቤ ጋርም መጠናዊ ግንኙነት አለን በማለት ሲናገሩ ሰምተናል።

በራሳቸው ኢሳት ሚዲያና ራዲዮ ደግሞ በተዘጋጁ ሆድ አደር ግለሰቦች ሃሳቡን በማስጠናትና የገንዘብ ድጎማ በመስጠት ያለምንም የፎቶግራፍም ሆነ የቪዲዮ መራጃ በተለያዩ ቦታዎች የተደሩጉ ወጊያዎች ላይ መማረካቸውን ፣ማቁሰላቸውንና መግደላቸውን በተለመደው የቅጥፈት ፖለቲካቸው አስደምጠውናል።

በቅርቡ ‘’በወገራ ችንፋስዝ ፣በገና ሲናሬ በተባለ ከተማ ውስጥ ድንገተኛ ውጊያ ከፍቶ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቁን የግምባሩ ምንጮች ገለጹ ‘’ የተባለው በአካባቢው ህዝብና ገበሬ በወያኔ ኢሃዴግ አስተዳደርና ግዞት ተማሮ በአመጽ ሆ ብሎ በመውጣት የፈጸመውን ህዝባዊ ዱላ የራሳቸው የትግል እንቅስቃሴ በማስመሰል በግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት የተቀነባበሩ የግዳይ ንጥቆሽ መሆኑን ከበቂ መረጃ ጋር ደርሰንበታል።

ይህንን ዓይነት የግንቦት 7 አመራር የመንደር ወሬ ቅጥፈት ሊበቃውና ልናስቆመው ይገባል።

የግንቦት 7 ድርጅት በተለያዩ ጊዚያት በሚዲያው ኢሳትና ራዲዮው በተለያዩ ጊዜያት አስመረቀናል በመካናይዝድ የተጠናከረ ጦር አለን በማለትና በምዕራብ ጎጃም 600,በደቡብ ጎንደር 500 የታጠቀ ሰራዊት አለን በማለት በየዱርና ገደሉ መሽጎ ያለውን ገበሬና ነጻነት ናፋቂ ሕዝባችንን በየጊዜው የእርጎ ባህር እያሳዩት ይገኛል።

በአንድ ወቅት ፊሽካው ተነፍቷል ያሰኙት እነኚሁ የትግሉ ጋሪጣ የሆኑት ጥቂት ግለሰቦች ማንነትና ስራቸውን የአስተናጋጅ ሃገርና የኢሕአግ ሰራዊት ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ መሆኑንን የዘነጉት በቁጥር አንድና ሁለት የሚባል ሰራዊት ቀርቶ ወሬ ነጋሪ የሌላቸው ምሁራን ተብዪ ግንቦቴዎች ገንዘብ ከመለመንና ከመወሻከት ያለፈ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቅም አጀንዳ የሌላቸው በደሞዝ የሚተዳደሩ ፣የሌሎችን የትግል እንቅስቃሴ በመውረስ የራሳቸው አስመስለው የሚናገሩ ጸረ ትግል አቋም ያላቸው አጋጣሚዎችን የሚጠቀሙ (opportunist) ናቸው።

የግንቦት ሰባቱ ቋሚ ደሞዝተኛና ተቀጣሪው አበበ ቦጋለ እጅግ የሚያሳዝን በታጋዮችና ነጻ አውጪዎች ስም በመነገድ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ከአሳዳሪው በተሰጠው የተለያየ የስልጣን ስም በመጠቀም የተስዉትን ታጋዮች ስም በማንሳት እጃችን አለበት፣እኛ ረድተናቸው ነው ፣አስታጥቀናቸው ነው፣ ጥይት ገዝተንላቸው እንጂ ከየት አመጡት ብሎ ሲናገር ስንሰማ የግንቦት 7 የታጋይ ጠላት ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር አብሮ የሚሰራ የሃገር ጠላት መሆኑን አረጋገጠልን እንጂ እንደ ሌሎቹ አላታለለንም።

አረ ለመሆኑ የአርበኛ ጎቢን አሟሟት በተመለከተ ዘመዶቹ ተገዝተው እንደገደሉት መረጃ የደረሰው የግንቦት 7 ቱ የህዝብ ግንኙነት እንዴት ነው ታዲያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዪን) ከኋላው አብሮት የነበረው የግንቦት 7ቱ እግረኛ ወያኔዎች ሳይመጡ ገና ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በተቃረቡበት ቦታ ላይ አብረው በማፈግፈግ ላይ እያሉ በተሰጠው ተልዕኮ ከጀርባው ተመቶ የተገደለውን ታሪክ እውነታ ያልሰማው?

ነው ወይስ ለገንዘብ መለመኛ እንዲያመቻቸው እራሱን አጠፋ መባሉን መክረውና ዘክረው ያዘጋጁት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ታጋዮች ቢሞቱ ወይም ቢገደሉ ተመሳሳይ ድርጅታዊ ቀመር (Formula) እንደሆነ አንባቢያን እንድትረዱልን እንፈልጋለን።

ወድ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊያንና አባላት እንዲሁም ግንቦት 7ን ሳታውቁት በአባልነት የምትንቀሳቀሱ እውነተኛ ነጻነት ፈላጊዎች!!

ነጻነት ገንዘብ በማሰባሰብና በቲፎዞ የሚመጣ አይደለም።

በየጊዜው ከህዝባችን በስማችን የተሰበሰበው ገንዘብ በአስተናጋጅ ሃገር ለሚገኘው ለኢሕአግ ሰራዊትም ሆነ በጎበዝ አለቆች ለሚመራው ሕዝባዊ ሰራዊት ግንቦት 7 ከተባለው ድርጅት የተሰጠው ድጎማም ሆነ የመሳሪያ ቁሳቁስ ዕርዳታ የተቸረ ያለመኖሩን እየገለጽን በስማችን የሚደረገው ውህደትም ሆነ ጥምረት የማይመለከተን መሆኑንን እየገለጽን ዶንያ ሙሉ ወሸት የትም አያደርስም ፣በህዝብ ሰም እየነገዳችሁ የትግሉ ጋሪጣ አትሁኑ የምንልበት ጊዜ አሁን ነው።

ሃገራችን ኢትዮጵያ ነጻ እንድትሆን በጋራ መስራትና በጋራ መታገል ጥያቄ የማያሻው መፍትሄ መሆኑን አውቀን በሃር ውስጥም ፣በውጪም የምትገኙ እውነተኛ የትግሉ አጋሮች ከመሰል የሃሰተኛ ቅስቀሳ ነጻ ወጥታችሁ ለሃገራችንና ሕዝባችን በአፋጣኝ እንድንደርስለት አበክረን እናሳውቃለን !

ሁሉንም ለማወቅ ለምትሹ ወገኖች በስራችንም ሆነ በትግላችን ተከዜን ሳይሻገሩ ድል የለም ይሁንና የግንቦት 7 ባለሟሎች በሁለገቡ ትግላችን ከወሬና ገንዘብ ከመሰብሰብ በስተቀር ድሮም አልነበሩም አሁንም የሉም

አንድነት ሃይል ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር 

 

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles