ኦሮሞ የሚለውን ቃል የፈጠረው "ክራፕፍ" ነው??


አዎን! በዚህ ግልብ የፌስቡክ በረንዳ ላይ እንደዚህ እየተባለ ሲጻፍ አያለሁ፡፡ ቢሆንም ነገሩ ፌዝና ተረት ነው፡፡ ክራፕፍ የሚባለው ሚሺነሪ "ኦሮሞ" ብሎ ፅፎ እንኳ አያውቅም፡፡ በየትኛውም የክራፕፍ መፅሐፍ ውስጥ እንደዚህ የሚል ቃል የለም፡፡ ክራፕፍ የሚታወቀው "ኦርማኒያ" በሚለው ስም የኦሮሞን ሀገር በመጥራቱ ነው፡፡ ይህንንም "ኦርማ" ከሚለው ቃል ነው የወሰደው፡፡ 
-----
"ኦሮሞ" ጥንትም የነበረ ስም ነው፡፡ ይህንን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ የጠቀሰው ደግሞ ታዋቂው እንግሊዛዊ ሀገር አሳሽ ሰር ዊሊያም ኮርንዋሊስ ሃሪስ ነው፡፡ ይህም የክራፕፍ መጽሐፍ ከመታተሙ ከ25 ዓመት በፊት በ1843 የተፈጸመ ነው (ብዙ የፌስቡክ መሃይማንና አሽቃባጮች እየደጋገሙ የሚጠቅሱት የክራፕፍ መጽሐፍ የታተመው በ1868 ነው)፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የምስራቅ አፍሪቃ ህዝቦችን አንትሮፖሎጂና ታሪክ በስፋት ያጠኑት እነ ጁልስ ቦረሊ፣ አንቶን ዲአባድ፣ ቪክቶር ፖሊሽኪ ህዝቡን ያስተዋወቁት በዚሁ ስም ነው፡፡ 
----
መከባበር መልካም ነገር ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከጥፋት ማዳን የሚቻለው ስንከባበር ብቻ ነው፡፡ በተለይ የህዝቦቻችንን የማንነት ምልክቶችና እሴቶች በሙሉ ልብ ማክበር ያስፈልጋል፡፡ ህዝብ ካልተከበረ ሀገር አይኖርም፡፡

ባለፈው ጊዜ ወዳጄ በውቀቱ ስዩም አንድ አሪፍ ምልከታ ጠቁሞን ነበር፡፡ አንድ ህዝብ "የኔ መጠሪያ ይሄ ነው" ካለ በቅንነት አክብረን መቀበል እንዳለብን ነግሮናል፡፡ ለኛም ሆነ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚሻለው መንገድ ይኸው ነው፡፡

 

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles