"ኢሳትን ገንዘባችንን ባለመስጠት ከአየር እናውርድ" ''ግንቦት7 ባለመደገፍ ከፖለቲካው መንደር እናስወግድ''' የሚለው ዘመቻ እንደቀጠለ ነው።

በአማራው አክቲቪስቶችና በሌሎች ተገፋን በሚሉ ተቃዋሚ ቡድኖች፣በግንቦት7 ላይ ከመነሻው ጀምሮ አካሄዱ ካላማራቸው ግሩቦችና በተለያየ ጊዜ ከድርጅቱ በወጡ ግለሰቦች የተቀነባበረውና የተጀመረው ዘመቻ ሳምንቱን በሙሉ በሶሻል ሚዲያዎች በፓልቶኮች በተለያዩ ከተሞች በሚሰራጩ የሎካል ራዲዮኖች ፣ዌብሳይቶች ሲካሄዱ ሰንብተዋል።ግንቦት7 እንዲህ የከረረ ተቃውሞ ሲገጥመው የመጀመሪያው ባይሆንም የአሁኑ ለየት የሚያረገው ሁኔታው የተቀነባበረና ከግንቦት7 ይመጣል ተብሎ የሚፈራውን ቡጢ የመከተና በድፍረት በግልጽ ተቃውሞ የተሰማበት ከዚህ በፊት በከፍተኛ ደረጃ ይደግፉና ይተባበሩ የነበሩ ግለሰቦች ሳይቀሩ በዘመቻው መሳተፋቸው ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የግንቦት7 ደጋፊዎች በዘመቻው የተሰማቸውን በገለጹ በት አባባል መረጃውን ለማቆም

ዛሬ "ኢሳትን ከአየር እናውርድ" በማለት ዘመቻ የጀመረ ቡድን፣ የሃሳብ ነፃነት ያልገባው ያልሰለጠነ "የተቃውሞ "ፖለቲከኛ ነገ እድሉ ገጥሞት ስልጣን ቢይዝ የአገሩን ሁሉ ዲሽ አውርዶ መዘፍዘፊያ ሳፋ እንደማያደርገው አለማመን አይቻልም።ሲሉ የግንቦት7 ደጋፊዎች ተችተው አልፈዋል።

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles