ተጨማሪ መረጃ ስለቴዲ አፍሮ ነገር - Daniel Berhane

 ተጨማሪ መረጃ ስለቴዲ አፍሮ ነገር፡-(ዜና ቢጤ ልጽፍ ነበር - ነገር ግን ጤናም መረጃም አልተሟላም፡፡ ስለዚህ ያለውን በጨረፍታ ላካፍላችሁ)፡፡

ሲጀመር ቴዲ አፍሮ - እነሻኪራ ባለፈው የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ላይ እንደዘፈኑት ዓይነት ዘፈን ለማዘጋጀት እንደተመረጠ አድርገው በመዘገብ ያሳሳቱን የአዲስ አበባ ጋዜጦች ናቸው፡፡

ካደረግሁት ንባብ እንደተረዳሁት፡- ፊፋ ለእያንዳንዱ የዓለም ዋንጫ ከሚያዘጋጀው ይፋዊ ዘፈን(official World Cup Anthem) በተጨማሪ፤ ተደራቢ ይፋዊ ያልሆኑ ሙዚቃዎችን(unofficial local versions) ለተወሰኑ ሀገሮች/አካባቢዎች የማዘጋጀት አሠራር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጀምሯል፡፡ [ፊፋ ሲባል ኮካኮላን አትርሱ - እንደጉድ የተጣበቁ ናቸው]

እና.... ለዚህ ለብራዚል የዓለም ዋንጫ ፊፋ አድማሱን በማስፋት 24 ይፋዊ ያልሆኑ አካባቢያዊ ሙዚቃዎችን(unofficial local versions) ለማካተት ወሰነ፡፡ [ዘፋኞቹ ዋናውን ይፋዊ(official version) ዘፈን መነሻ በማድረግ - በተወሰነ ደረጃ በማዳቀል መሥራት ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡]

ከ24ቱ አንዷ ኢትዮጲያ ሆነች፡፡ ለምን ኢትዮጲያን? አላውቅም! ግምት? አልገምትም፡፡ [ካስገደዳችሁኝ - በኢኮኖሚ ወሳኝ ሀገር እየሆንን በመምጣታችን ይሆናል:: እንግዲህ በግድ ገምት ብላችሁ - እንደገና ግምቴን መተቸት አትችሉም፡፡]

እና ከዚያ.... ከኢትዮጲያ የትኛው አርቲስት ይሁን? የሚለው በምን አሠራር እንደተወሰነ እስካሁን አልታወቀም፤ ነገርግን ግልጽ ባልሆነ መንገድ የተመረጠው ቴዲ - ግልጽ ባልሆነ መንገድ ተሰናብቷል፡፡

የበደሌ/ሀይከን ቢራ ፕሮግራም ሲሰረዝ በአደባባይ ምንም ያላለው ቴዲ - በዚህ ጉዳይ ግን በየ FM ራዲዮ እሰጥ አገባ ጀምሯል፡፡ምናልባት..... ምናልባት.....፣ በደሌ ፕሮግራሙን ሲሰርዝ በነፃ (አፍ ማስያዣ) አንድ ሚሊየን ብር እንደሰጠው፤ ኮካ ኮላም ተመሳሳይ ገንዘብ አልከፍል ብሎ ይሆን? አላውቅም አልኳችሁ! በግድ ግምት ውስጥ አታስገቡኝ፡፡

በዚህ ሊወቀስ የሚገባው ግን ኮካ ድርጅት ነው፡፡በጓሮ(በድብቅ) መምረጥ -በጓሮ መሠረዝ ምን አስፈለገ?
ለማንኛውም ይሄ ዕድል፡- ኢትዮጲያ ለቴዲ አፍሮ ያመጣችለት እንጂ፤ ቴዲ አፍሮ ለኢትዮጲያ ያመጣው አይደለም፡፡ አጋጣሚውን በአግባቡ ባለመጠቀሙ ሀገሪቱ መጎዳትዋ አልቀረም፡፡

ለሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ - ቴዲ አፍሮ ይበስልና ለኢትዮጲያ የሚዘጋጀውን unofficial local version ይዘፍን ይሆናል፡፡ ወይም...ወይም ታማኝ በየነን መጋበዝ ነው፡፡

 

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles