መለስ Vs ጃዋር Hirut Hailu

 

 

አመድ በዱቄት ይስቃል አሉ!
ህወሓታውያን ጃዋርን አገር እንደሚገነጥል ፣ አክራሪ ሙስሊም እንደሆነ እና አደገኛ ግለሰብ መሆኑን ያቻሉትን ያክል ያለመታከት በህዝቡ ላይ ፍራቻን ለማስፈን በሚዲያቸው እየሰሩበት ነው። ነገር ግን፦

※ ኤርትራ እንድትገነጠል ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን እየወጋ 4ኪሎ የደረደው ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ኢትዮጵያን ያለባህር በር ያስቀራት ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※በጎንደር በኩል ያለውን የኢትዮጵያን ለም መሬት(1600 ኪሜ) ለሱዳን ይገባታል ብሎ ቆርሶ የሰጠ ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ኢትዮጵያን በብሄር እና በሀይማኖት ከፋፍሎ እርስ በእርስ እንዲባላ ያደረገ ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ ኢትዮጵያን ያለ ብሔራዊ ቋንቋ ያስቀራት ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ የኢትዮጵያ ህዝብ ከአገራዊ ቅርሶቹ አንዱ ነው ብሎ የሚመካበትን የአክሱምን ሀውልት" የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው" ብሎ በአደባባይ የተናገረው ጃዋር ሳይሆን ዘረኛው መለስ ነው እኮ?!

※ በአያቶቻችን እና በቅድመ አያቶቻችን ደምና አጥንት የተገነባውን ሰንደቅ አላማችንን "ጨርቅ" ብሎ ያንቋሸሸ ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ሰንደቅ አላማችንን መቀሌ ላይ ለአህያ አስለብሶ እስታድየም ውስጥ እንዲዞር ያደረገ ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ምናምን አስከብረናል እየተባለ በሚደሰኮርላት ኢትዮጵያ ነገር ግን ካሉት 82 ብሔሮች ውስጥ አንዱን የትግራይን ህዝብ ብቻ በመምረጥ እንኳን ከእናንተ "የወርቅ ዘር" የተፈጠርኩ እንኳን የሌሎቹ አልሆንኩ በማለት ለቀሪው ኢትዮጵያዊ ለመለስ ምንም አለመሆናችን፣ ባእድ መሆናችንን፣ ጠላት መሆናችንን በአደባባይ የነገረን ጃዋር ሳይሆን መለስ ነው እኮ?!

※መለስ እና ግብረ አበሮቹ ለትግራይ ህዝብ ቆመናል፣ የትግራይ ህዝብ ተበድሏል በማለት ከ41 አመት በፊት ትግራይን ለመገንጠል ደደቢት በረሀ ገቡ። ጃዋር ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ተበድሏል፣ስለ ኦሮሞ ህዝብ ቆሜያለሁ ብሏል። እናንተ ለትግራይ ህዝብ ቆመናል ካላችሁ ጃዋር ለኦሮሞ ህዝብ ቢቆም ሀጢያቱ ምኑ ላይ ነው?! ኧረ ስንቱን ልዘርዝረው?!

ለእናንተ ሲሆን የምታደርጉት ነገር በሙሉ ፍፁም ፃድቅ ነው። እናንተው የምታደርጉትን ሌላው ሲያደርገው ለምንድን ነው ሀጢያት የሚሆነው?!

ለማንኛውም በየትኛውም መመዘኛ እናንተ ስለኢትዮጵያዊነት እና ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ለማውራት የሞራል ብቃቱ የላችሁምና ጃዋር ምናምን ግብፅ ቅብርጥሴ እያላችሁ አታደንቁሩን የሚሰማችሁ የለምና!!!

NB. ጃዋርን ቅዱስ ለማድረግ ሳይሆን ለደደቢቶቹ ለትግራይ ነፃ አውጪወች መልስ ለመስጠት ነው!

© Hirut Hailu

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles